Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሴቪያ የዩሮፓ ሊግ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዩሮፓ ሊግ ትናንት ምሽት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በጀርመን ኮሎኝ የተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ የስፔኑን ሴቪያ ከጣሊያኑ ኢንተር ሚላን ተገናኝተው ሴቪያ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ዋንጫውን አንስቷል፡፡ በጨዋታው ኢንተር ሚላን በሮሜሉ ሉካኩ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል ቀዳሚ መሆን ችሎ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ ደ ዮንግ በተከታታይ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች እንዲሁም ሉካኩ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ጎል ሲቪያ ባለድል ሆኗል፡፡ ዲያጎ ጎዲን የኢንተር ሚላንን ሁለተኛ ጎል ቢያስቆጥርም ቡድኑን…
Read More...

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ሊሸጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን በቴሌቪዥን ማስተላለፍ ለሚችሉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል፡፡ በሀገራችን የሚካሄደው የወንዶች እግር ኳስ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ16 ክለቦች መካከል በሜዳ እና ከሜዳ ውጭ በሚል የውድድር ፎርማት ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የሊጉ ኩባንያ በቀጣይ…

ሮናልድ ኪዩመን ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት ተረከበ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፔኑ ባርሴሎና ሮናልድ ኪዩመንን አሰልጣኙ አድርጎ ሾሟል፡፡ የካታላኑ ክለብ የቀድሞ አሰልጣኙ ኪኬ ሴቲዬንን ከቻምፒየንስ ሊጉ ሽንፈት በኋላ አሰናበቷል፡፡ ይህን ተከትሎም የቀድሞው የክለቡን ተጫዋች ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡ ኪዩመን የኔዘርላንድስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ከ16 አመት በኋላ ተሰበረ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ5 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ትናንት ማታ በዑጋንዳዊው አትሌት ቼፕቴጌ ተሻሽሏል፡፡ ጆሹዋ ቼፕቴጌ ትናንት ምሽት በሞናኮ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር የ5 ሺህ ሜትሩን ክብረ ወሰን በሁለት ሰከንዶች አሻሽሎታል፡፡ አትሌቱ ርቀቱን 12 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ከ36 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ…

በቻምፒየንስ ሊጉ ሙኒክ ባርሴሎናን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸንፎታል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በተደረገ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ባርሴሎና ከባድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ በሊዝበን በተደረገው ጨዋታ የጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ባርሴሎናን 8 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፎታል፡፡ በጨዋታው ቶማስ ሙለር እና ተቀይሮ የገባው ፊሊፔ ኮቲንሆ ለሙኒክ ሁለት ሁለት ጎሎችን አስቆጥረዋል፡፡ ቀሪዎቹን…

ዊሊያን በሶስት አመታት ውል አርሰናልን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚላዊው የመስመር አማካር ዊሊያን የሰሜን ለንደኑን የእግር ኳስ ክለብ አርሰናልን ተቀላቀለ፡፡ ዊሊያን የምዕራብ ለንደኑን እግር ኳስ ክለብ ቼልሲን በመልቀቅ ወደ አርሰናል በነጻ ዝውውር አምርቷል፡፡ የ32 አመቱ ዊሊያን በአርሰናል ለሶስት አመታት ለመቆየት መስማማቱም ነው የተነገረው፡፡ ዊሊያን በፈረንጆቹ 2013…

በቻምፒየንስ ሊጉ አር ቢ ሌፕዚግ የግማሽ ፍጻሜተፋላሚ መሆኑን አረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ተካሄዷል፡፡ አር ቢ ሌፕዚግ እና አትሌቲኮ ማድሪድን ባገናኘው ጨዋታ የጀርመኑ ክለብ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ በፖርቹጋል ሊዝበን በተደረገው በዚህ ጨዋታ አር ቢ ሌፕዚግ ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ኦልሞ እና አዳምስ ለአርቢ…