ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ እና ባህርዳር ከነማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ ከተሞች ተካሂደዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ ቡና፣ ሀዋሳ ከተማ፣ ባህርዳር ከነማ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል።
ወላይታ ድቻን በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የኢትዮጵያ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ሃብታሙ ታደሰ እና አቡበከር ናስር ሲያስቆጥሩ፥ የወላይታ ድቻን ብቸኛ ግብ ደግሞ ባዬ ገዛኸኝ አስቆጥሯል።
ወደ ሀዋሳ በማቅናት ሀዋሳ ከተማን የገጠመው ፋሲል ከነማ ደግሞ 3…
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ሰበታ ከተማ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል።
ሰበታ ከተማን በሜዳው ያስተናገደው ሲዳማ ቡና ሰበታ ከተማን 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሲዳማን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎልም ይገዙ ቦጋለ በ56ተኛው ደቂቃ ማስቆጠር ችሏል።
የሊጉ በርከት ያሉ ጨዋታዎችም ነገ የሚካሄዱ ይሆናል።
በፕሪሚየር ሊጉ ሃዲያ ሆሳዕና ጅማ አባጅፋርን አሸነፈ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሀ ግብር ዛሬ አንድ ጨዋታ ተካሄዷል።
በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና በጅማ አባጅፋርን በሃዋሳ ስታዲየም አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የሃዲያ ሆሳዕናን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል አዩብ በቀታ ማስቆጠር ችሏል።
ሌሎች የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ…
አትሌት አባብል የሻነህ በግማሽ ማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ሰበረች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ራስ አል ከሂማህ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አባብል የሻነህ የዓለም ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች።
አትሌት አባብል በፈረንጆቹ 2017 ኬንያዊቷ አትሌት ጆይስሊን ጄፕኮስጊ በቫሌንሺያ የያዘችውን ክብረ ወሰን በ20 ሰከንድ በማሻሻል አሸንፋለች።
በውድድሩ አትሌት…
በፈረንሳይ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፈረንሳይ ሌቪን ትናንት ምሽት በተካሄደ የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
ኢትዮጵያውያኑ በ1 ሺህ 500 ሜትር በወንድ እና ሴት እንዲሁም በ3 ሺህ ሜትር ወንዶች በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል።
በዚህ መሰረት በወንዶች 3 ሺህ ሜትር አትሌት ጌትነት ዋለ 7 ደቂቃ፣ ከ32 ሰከንድ፣…
የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በካሜሮን አዘጋጅነት የሚካሄደው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡
ከሁለት ወራት በኃላ ለሚጀመረው የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዉን ያለፉ ሀገራት የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል::
በዚህም በምድብ አንድ ካሜሮን፣ ማሊ፣ቡሪኪና ፋሶ እና ዚምባቡዌ ሲደለደሉ በምድብ ሁለት ሊቢያ ፣ዲሚክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ኮንጎ…