ስፓርት
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ከማንቼስተር ዩናይትድ አምባሳደርነት ሊነሱ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ የቀድሞው ስኬታማ አሰልጣኝና ባለፉት ዓመታት የቡድኑ ዓለም አቀፍ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በዓመቱ መጨረሻ ከኃላፊነታቸው እንደሚሰናበቱ ተሰምቷል፡፡
ሰር አሌክስ ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ ቀያይ ሰይጣኖቹን በዓለም አቀፍ አምባሳደርነት እንዲሁም ክለቡን በዳይሬክተርነት በማገልገላቸው በርካታ ሚሊየን ፓውንድ እንደተከፈላቸውም ተገልጿል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ለእርሳቸው የሚከፍለውን ገንዘብ በማስቀረት ማንቼስተር ዩናይትድን ለማደራጀትና ለማጠናከር እንዲውል…
Read More...
በቺካጎ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ቺካጎ በተካሄደው "ቺካጎ ማራቶን 2024 "የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ 2ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡
በወንዶች ማራቶን ውድድር ኬንያዊው አትሌት ጆን ኬሪ 2 ሰዓት ከ2 ደቂቃ ከ42 ሴኮንድ በመግባት በ1ኛነት ሲያጠናቅቅ ኢትዮጵያዊው መሐመድ ኢሳ ደግሞ በ2 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ከ39 ሴኮንድ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጊኒ አቻው ጋር ምሽት 1 ሰዓት ላይ በአቢጃን ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ለዚህም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አስቀድሞ ወደ ኮትዲቯር አቢጃን የተጓዘ ሲሆን÷ለዛሬው ጨዋታ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱ ተጠቁሟል፡፡
በጨዋታው አማካዩ ቢኒያም በላይ በጉዳት ከመጨረሻዎቹ ልምምድ ውጭ መሆኑ…
ከ4ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ያሉት የፕሪሚየርሊጉ ጨዋታዎች ማስተካከያ ተደረገባቸው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ4ኛ እስከ 13ኛ ሳምንት ባሉ መርሐ-ግብሮች የኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ ጨዋታዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ አክሲዮን ማኅበር አስታወቀ፡፡
የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ሳምንት መርሐ-ግብሮች በድሬዳዋ ስታዲየም ከተደረጉ በኋላ በብሔራዊ ቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት…
ኧርሊንግ ሃላንድ የኖርዌይ ብሄራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖርዌጂያኑ የማንቼስተር ሲቲ አጥቂ ኧርሊንግ ሃላንድ በ36 ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ባስቆጠራቸው ግቦች የሀገሩ የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ለመሆን በቅቷል፡፡
የ24 ዓመቱ አጥቂ ትናንት ምሽት በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ኖርዌይ ስሎቫኒያን 3 ለ 0 ባሸነፈችበት ጨዋታ 2 ግቦችን በማስቆጠር ሪከርዱን የግሉ ማድረግ ችሏል፡፡…
ኢትዮጵያ በአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና 3ኛውን የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ ኤልዶሬት እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና ድብልቅ ውድድር ኢትዮጵያ 3ኛውን የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
የአፍሪካ የብስክሌት ሻምፒዮና በኬንያ ኤልዶሬት ከትናንት ጀምሮ እየተካሄደ እንደሚገኝ የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
የቀድሞ የሼፊልድ ዩናይትድ ተከላካይ ጆርጅ ባልዶክ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞ የሼፊልድ ዩናይትድ ተከላካይ እና አሁን ላይ ለግሪኩ ፓናቲናይኮስ በመጫወት ላይ የነበረው ጆርጅ ባልዶክ በ31 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ባልዶክ አቴንስ በሚገኘተው መኖሪያ ቤቱ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ሕይወቱ አልፎ መገኘቱ ተነግሯል፡፡
ፖሊስ የተጫዋቹን ሞት መንስኤ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጹን ቢቢሲ…