Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ዋልያዎቹ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከግብፅ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2026 የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አምስተኛ ጨዋታውን ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያከናውናል። ዋልያዎቹ በምድቡ ካደረጓቸው አራት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ በመያዝ በምድቡ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፤ ተጋጣሚያቸው የግብፅ ብሔራዊ ቡድን በ10 ነጥብ ምድቡን በበላይነት እየመራ ይገኛል። ካዛብላንካ በሚገኘው ላርቢ ዛውሊ ስታዲየም ሌሊት 6 ሠዓት ላይ የሚደረገውን የሁለቱን ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ሞሪሸሳዊው ዳኛ ፓትሪስ ሚላዛር በመሐል ዳኝነት ይመሩታል። የኢትዮጵያ…
Read More...

15 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች የሚሳተፉበት ሜሪ ጆይ የ5 ኪሜ ሩጫ መጋቢት 28 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2017 (ኤፍኤምሲ) "አረጋውያንን እመግባለሁ፤ ጤንነቴን እጠብቃለሁ" በሚል መሪ ቃል የበጎ አድራጎት ገቢ ማሰባሰቢያ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር መጋቢት 28/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው። ሁነቱን አስመልክቶ አዘጋጆቹ ሜሪጆይ ኢትዮጵያ እና ብራይት ኤቨንትስ በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም ‹‹ሜሪ ጆይ የ5…

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እና ጥሩነሺ ዲባባ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን …

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኩራት የሆኑት አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና በአጭር እና በረጅም ርቀት እንዲሁም ጥሩነሺ ዲባባ የታዳጊዎች እና የአዋቂዎችን ውድድር በአንድ ጊዜ በማሸነፍ ከ20 ዓመታት በፊት በዛሬዋ ቀን ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል፡፡ አትሌት ቀነኒሳ የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮናን በአጭር እና በረጅም ርቀት…

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ወደ ቻይና አቀና

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ ከመጋቢት 21 እስከ 23 ቀን 2025 በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ወደ ቻይና ናንጂንግ ሌሊት ላይ አቅንቷል። ቡድኑ 12 አትሌቶች፣ ሁለት አሰልጣኞች፣ አንድ ቡድን መሪ፣ አንድ የቴክኒክ ቡድን መሪ፣ አንድ ከፍተኛ የህክምና ባለሙያ እና አንድ ፊዝዮቴራፒስት…

በለንደን ደርቢ አርሰናል ቼልሲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 29ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር አርሰናል በሜዳው ኢምሬትስ ቼልሲን አስተናግዶ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሚኬል ሜሪኖ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከአስራ ሁለት ጨዋታዎች በኋላ የማዕዘን ምት ግብ አስቆጥሯል።…

በባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2025 የባርሴሎና ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡ በወንዶች የማራቶን ውድድር አትሌት ተስፋዬ ድሪባ በአንደኝት ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ርቀቱን ለመጨረስም 2 ሠዓት ከ4 ደቂቃ ከ13 ሰከንድ ፈጅቶበታል፡፡ በዚሁ ውድድር አትሌት ተስፋዬን በመከተል ኬንያውያን አትሌቶች ከ2ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው…

የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድርን አትሌት ብሬነሽ ደሴ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡ በውድድሩ አትሌት አብዙ ከበደ 2ኛ እንዲሁም መቅደስ ሽመልስ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተከታትለው ገብተዋል። የ2017 ዓ.ም ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ…