ስፓርት
ተጠባቂው የዛሬ ምሽት የቦክስ ፍልሚያ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ዛሬ ምሽት በአሜሪካ ቴክሳስ አርሊንግተን ይካሄዳል፡፡
ከዓመታት በፊት ቀጠሮ በተያዘለት ፍልሚያ የዓለም የቦክስ ባለታሪኩ ማይክ ታይሰን እና በ1997 ማይክ ታይሰን ልደቱን ካከበረለት ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ እና ዩቲዩበር ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር ይደረጋል፡፡
ከውድድሩ አስቀድሞው አንጋፋው ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን “ታይሰን አላረጀም አሁንም ጠንካራ ቡጢውን ተጋጣሚ ላይ ማሳረፍ የሚችል አቅም አለው” ሲል…
Read More...
አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ የ2024 ተስፋ ከሚጣልባቸው ሦስት ሴት አትሌቶች ውስጥ ተካተተች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ የ2024 ተስፋ ከሚጣልባቸው ሦስት ሴት አትሌቶች ውስጥ ተካትታለች፡፡
በዘንድሮ የዓለም አትሌቲክስ ምርጥ ከ20 ዓመት በታች ወይንም ተስፋ የሚጣልባቸው አትሌቶችን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስተዋውቋል፡፡
በዚህም አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ በሴቶች የ2024 ተስፈኛ ኮከብ አትሌት ሽልማት የመጨረሻ ሦስት…
ሩድ ቫኒስትሮይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሆላንዳዊው የቀድሞ የእግር ኳስ ኮከብ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያይቷል፡፡
የ48 ዓመቱ የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ በሁለት ዓመት የኮንትራት ውል የማንቼስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝ ለመሆን መስማማቱ ይታወሳል፡፡
የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን ስንብት ተከትሎም ቫን ኒስትሮይ ማንቼስተር…
ማንቼስተር ዩናይትድ ሌስተር ሲቲን 3 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ11ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በተመሳሳይ 11 ሠዓት ላይ ሦስት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡
በዚሁ መሠረት በሜዳው ሌስተር ሲቲን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በሌላ በኩል ቶተንሃም ሆትስፐር በኢፕስዊች ታውን 2 ለ 1 እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት በኒውካስል ዩናይትድ 3 ለ1 ተሸንፈዋል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን ተሸንፏል፡፡
ምሽት 2፡30 በተደረገው ጨዋታ ብራይተን ማንቼስተር ሲቲን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የብራይተንን ግቦች ዣኦ ፔድሮ እና ማት ኦሪሊይ ሲያስቆጥሩ የማንቼስተር ሲቲን ብቸኛ ግብ ደግሞ ኧርሊንግ ሃላንድ…
ዎልቭስ፣ ብሬንት ፎርድና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተደረጉ የ11ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዎልቭስ፣ ብሬንት ፎርድና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋ፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተደረጉ 4 ጨዋታዎች ዎልቭስ ሳውዝ ሃፕተንን፣ ፉልሃም ክሪስታል ፓላስን በተመሳሳይ 2 ለ 0 ሲያሸንፉ ብሬንትፎርድ ደግሞ ቦርንማውዝን 3 ለ 2 ረትቷል፡፡…
ዋሊያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከሁለት ሳምንት በኋላ ያደርጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንበ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ እና ሥድስተኛ የምድብ ጨዋታዎቹን ያደርጋል፡፡
በወጣው መርሐ-ግብር መሠረትም ዋሊያዎቹ ሕዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከታንዛኒያ አቻቸው ጋር እንደሚጫወቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
እንዲሁም ሕዳር 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከዲሞክራቲክ…