ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ሲቲ ሲሸነፍ ሊቨርፑል አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ ሲሸነፍ ሊቨርፑል ድል ቀንቶታል፡፡
ወደ ቫይታሊቲ ስታዲየም ያቀናው የሊጉ መሪ ማንቼስተር ሲቲ በቦርንማውዝ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡
ለቦርንማውዝ ግቦቹን ሴሜኞ እና ኢቫኒልሰን ሲያስቆጥሩ÷ጆስኮ ግቫርዲዮል ደግሞ ሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ከመመራት ተነስቶ ብራይተንን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ÷ኮዲ ጋክፖ እና ሞሃመድ ሳላህ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡…
Read More...
አርሰናል በኒውካስል ዩናይትድ ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን የገጠመው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
የኒውካስል ዩናይትድን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አሌክሳንደር ኢሳክ 12ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የጨዋታ መርሐ ግብሩ ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ የሊጉ መሪ…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ10ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አርሰናል ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ ኒውካስል ዩናይትድን የሚገጥምበት ተጠባቂ ጨዋታ ቀን 9:30 ይደረጋል።
ምሽት 12:00 ላይ የሊጉ መሪ ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ በርንማውዝን የሚገጥም ሲሆን÷…
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ።
ምሽት 1 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በረከት ሳሙኤል (በራስ ላይ) እና ኢዮብ ገብረማርያም ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ሀዋሳ ከተማን ከሽንፈት…
ወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሊግ እንዲጫዎት ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ2017 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተሰረዘው ወልቂጤ ከተማ በከፍተኛ ሊግ እንዲጫዎት መወሰኑን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
ወልቂጤ ከተማ ለ2017 የውድድር ዘመን የክለብ ላይሰንሲንግ ምዝገባ እና ሌሎች የተቀመጡ መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ከፕሪሚየር ሊጉ መሰረዙ ይታወሳል፡፡
ክለቡ የውድድር…
ሩበን አሞሪም የማንቼስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማንቼስተር ዩናይትድን በዋና አሰልጣኝነት እንዲመሩ በይፋ ተሹመዋል፡፡
በስምምነቱ መሠረት አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በኦልትራፎድ በፈረንጆቹ እስከ 2027 የሚያቆያቸውን ኮንትራት ፈርመዋል፡፡
ሆላንዳዊው ሩድ ቫል ኒስትሮይ በምክትል አሰልጣኝነት በቀያይ ሰይጣኖቹ ቤት እንደሚቀጥልም ነው…
ባሕር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሣምንት መርሐ-ግብር ባሕር ዳር ከተማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸነፈ፡፡
የባሕር ዳር ከተማን ግቦችም ፍሬው ሰለሞን እና ፍጹም ዓለሙ አስቆጥረዋል፡፡
በተመሳሳይ 1 ሠዓት ላይ በተካሄደው የዛሬ መርሐ-ግብር ዎላይታ ድቻ ሀድያ ሆሳዕናን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ካርሎስ ዳምጠው በ67ኛው ደቂቃ ኳሷን…