ስፓርት
መቻል ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋል፡፡
የመቻልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አብዱ ሙተለቡ በ86ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ሰዓት ላይ ድሬደዋ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በተመሳሳይ 12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ድሬደዋ ከተማ ተመስገን ደረሰ ባስቆጠራት ጎል ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
Read More...
17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ መካሄድ ይጀምራሉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 24 ሀገራት የሚሳተፉበት የ2024 የአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ አስተናጋጇ ጀርመን ከስኮትላንድ በሚያደርጉት የመክፈቻ ጨዋታ ይጀመራል፡፡
ጨዋታው ሲቀጥል ነገ ቀን 10 ሠዓት ላይ ሀንጋሪ ከስዊዘርላንድ፣ ምሽት 1 ሠዓት ላይ ስፔን ከክሮሽያ እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ላይ ጣልያን ከአልባኒያ ይጫወታሉ፡፡…
ሊዮኔል ሜሲ የእግር ኳስ ህይወቱን በአሜሪካው ክለብ ማጠናቀቅ እንደሚፈልግ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ የእግር ኳስ ህይወቱን በአሜሪካው ኢንተር ማያሚ ክለብ ማጠናቀቀቅ እንደሚፈልግ አስታወቀ፡፡
የ8 ጊዜ ባለንዶር አሸናፊው ሜሲ የፈረንሳዩን ክለብ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን በመልቀቅ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወደ አሜሪካ ማቅናቱ ይታወሳል፡፡
“ኢንተር ማያሚ የመጨረሻው ክለቤ ይሆናል ብዬ አስባለሁ” ሲል…
ህር ዳር ከተማና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የባህር ዳር ከተማን ግቦች ፀጋዬ አበራና ያብስራ ተስፋዬ አስቆጥረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ግቦች ደግሞ አዲስ ግደይ…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ27ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ወደ ውድድር ይመለሳል።
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከባህር ዳር ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይጫወታሉ።
በሌላኛው የ27ኛ ሳምንት ጨዋታ…
40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ሰኔ 30 ይካሄዳል- ፌደሬሽኑ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰኔ 16 ቀን 2016 ሊካሄድ የነበረው 40ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ወደ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም መራዘሙን አትሌቲክስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡
በተመሳሳይ ከሰኔ 11 እስከ 15 ቀን 2016 ሊካሄድ የነበረው 12ኛው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሰኔ 25 እስከ 29 ቀን እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡…
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቫር ሥራ ላይ መዋሉ እንዲቀጥል ወሰኑ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በቪዲዮ የተደገፈ ዳኝነት (ቫር) በሚቀጥለው የውድድር ዘመንም ሥራ ላይ መዋሉ እንዲቀጥል ወሰኑ፡፡
የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 20 ክለቦች ቫር ሥራ ላይ መዋሉ ‘‘ይቀጥል ወይስ ይቋረጥ?’’ በሚል ሀሳብ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ መሰረት 19ኙ ክለቦች ቫር ሥራ ላይ መዋሉን እንዲቀጥል…