Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ አገደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ከማሰልጠን ተግባራቸው በጊዜዊነት አግዷል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ስራ አመራር ቦርድ ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የዋናውን ቡድን እንቅስቃሴ ገምግሟል፡፡ በዚህም አሠልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የዋናው ቡድን ዋና አሠልጣኝ እና አሠልጣኝ ውብሸት ደሳለኝ የበረኞች አሠልጣኝ ተለዋጭ መመሪያ እስኪሰጥ ድረስ ከማሰልጠን ተግባራቸው ታግደው እንዲቆዩ ወስኗል። በምትካቸውም አሠልጣኝ ደረጀ…
Read More...

ጁለን ሎፔቴጉይ የዌስትሃም አሰልጣኝ ለመሆን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው አሰልጣኝ ጁለን ሎፔቴጉይ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ የዌስትሃም ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ተስማምተዋል፡፡ ስምምነቱ ተፈጻሚ ከሆነም የ57 ዓመቱ የቀድሞ የዎልቭስ አሰልጣኝ በድጋሚ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡ የመዶሻዎቹ አለቃ ዴቪድ ሞይስ ዌስትሃም ባለፉት 9 ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ብቻ ማሸንፉ እና…

በፕራግ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ የፕራግ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ። በወንዶች አትሌት ለሚ ብርሃኑ 2፡08፡45 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ፤ በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሄርጳሳ ነጋሳ እና አባይነህ ደጉ አምስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን…

ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት ፋሲል ከነማ ሀድያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ምሽት 12 ሠዓት ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው የፋሲል ከነማን ጎሎች ዣቪየር ሙሉ እና ምኞት ደበበ አስቆጥረዋል፡፡ እንዲሁም የሀድያ ሆሳዕናን ብቸኛ ጎል ደግሞ ዳዋ ሆጤሳ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስልና ኖቲንግሃም ፎረስት ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ36ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኒውካስል እና ኖቲንግሃም ፎረስት ተጋጣሚዎቻቸውን ሲያሸንፉ ብሬንትፎርድ ከፉልሃም አቻ ተለያይቷል፡፡ በዚህም ኒውካስል በርንሌይን 4 ለ1 እንዲሁም ኖቲንግሃም ፎረስት ሸፊልድ ዩናይትድን 3 ለ1 ረትተዋል፡፡ ብሬንትፎርድ እና ፉልሃም ደግሞ ያለምንም ጎል አቻ ተለያይተዋል፡፡

ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 2 ለ 1 አሸነፈ፡፡ የሲዳማ ቡናን ጎሎች ይስሃቅ ካኖ እና ማይክል ኪፕሮቪ ሲያስቆጥሩ÷ የወላይታ ድቻን ጎል ዘላለም አባተ ማስቀጠር ችሏል፡፡ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እየተካሄደ የሚገኘው የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት ጨዋታ…

አርሰናል የዋንጫ ተፋላሚነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርሰናል በርንማውዝን 3 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ተፋላሚነቱን አጠናክሯል፡፡ በ36ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በርንማውዝን በረታበት ጨዋታ ቡካዮ ሳካ፣ ትሮሳርድ እና ራይስ ጎሎቹን ማስቆጠር ችለዋል፡፡ መድፈኞቹ ዛሬ ማሸነፋቸውን ተከትሎም ነጥባቸውን 83 በማድረስ ፕሪሚየር ሊጉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡