ስፓርት
የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የካሜሩን አቻውን 3 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በምድብ ሦስት የሚገኙት ሴኔጋል እና ካሜሩን ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
ብሔራዊ ቡድኖቹ ያደረጉትን የምድብ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ÷ እስማኤል ሳር በ16ኛው፣ ሀቢብ ዲያሎ በ71ኛው እና ሳዲዮ ማኔ በ95ኛው ደቂቃ ከመረብ ባሳረፏቸው ጎሎች ሴኔጋል ድል አድርጋለች፡፡
የካሜሩንን የማስተዛዘኛ ጎል ደግሞ ቻርለስ ካስቴሌቶ በ83ኛ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡
በመጀመሪያው አጋማሽ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ ደግሞ የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን በኳስ ቁጥጥር ብልጫ…
Read More...
ኬፕ ቨርዴ ወደ ጥሎ ማለፉ ተቀላቀለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ኬፕ ቨርዴ ወደ ጥሎ ማለፉ የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡
በዛሬው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ሞዛምቢክን 3 ለ 0 አሸንፋለች፡፡
ጎሎቹንም÷ ቤቤ፣ ያን ሜንዴስ እና ኬቪን ሌኒ አስቆጥረዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ኬፕ ቨርዴ ጋናን 2 ለ 1 መርታቷ ይታወሳል፡፡…
የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ አይቬሪኮስት በናይጄሪያ ተሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ አይቬሪኮስት በናይጄሪያ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸነፈች፡፡
የናይጄሪያን የአሸናፊነት ጎል ዊሊያም ትሮስት ኤኮንግ በ55ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡
ቀደም ብሎ ከዚህ ምድብ በተደረገ ጨዋታ ጊኒ ቢሳው በኢኳቶሪያል ጊኒ 4 ለ 2 ተሸንፋለች፡፡
በምድብ ሁለት ምሽት 5 ሰዓት ላይ ግብጽ…
በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥሯል፡፡
በተመሳሳይ ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሻሸመኔ ከተማ ሀምበሪቾ ዱራሜን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በፕሪሚየር ሊጉ የ11ኛ ሳምንት መርሐ…
በአፍሪካ ዋንጫ ኢኳቶሪያል ጊኒ- ጊኒ ቢሳውን 4 ለ 2 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ኢኳቶሪያል ጊኒ- ጊኒ ቢሳውን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፈች፡፡
የአፍሪካ ዋንጫ የ2ኛ ዙር የምድብ ጨዋታ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 2 ሰዓት ላይ ኮቲዲቯር ከናይጄሪያ እንዲሁም 5 ሰዓት ላይ ግብጽ ከጋና የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ሞሮኮ ታንዛኒያን 3 ለ 0 አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በምድብ ስድስት የሚገኙት ሞሮኮ እና ታንዛኒያ ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡
ሮማን ሳዩስ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ለእረፍት የወጣችው ሞሮኮ÷ በሁለተኛው አጋማሽ ኡናሂ እና የሱፍ ኤል ነስሪ ባስቆጠሯቸው ተጨማሪ ጎሎች ጨዋታውን 3 ለ 0 ረትታለች፡፡
በ70ኛው ደቂቃ ኖቫቲስ ሚሮሺን በቀይ ካርድ ያጣችው…
መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
9፡00 ሠዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማን የገጠመው መቻል ከንዓን ማርክነህ እና በኃይሉ ግርማ ባስቆጠሯቸው ጎሎች 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
እንዲሁም 12፡00 ሠዓት ላይ ኢትዮጵያ መድንን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመመራት…