ስፓርት
በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ለፍጻሜ ደረሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዋንጫ ሀድያ ሆሳዕና እና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡
በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ከኢትዮጵያ መድን ጋር የተጫወተው ሃድያ ሆሳዕና በመለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ማለፉን አረጋግጧል።
በተመሳሳይ ቅዱስ ጊዮርጊስን የገጠመው ኢትዮጵያ ቡና በመለያ ምት 5 ለ 4 በማሸነፍ የዋንጫ ተፋላሚ መሆን ችሏል፡፡
በ17ኛ የአዲስ አበባ ዋንጫ በግማሽ ፍጻሜ የተሸነፉት ኢትዮጵያ መድን እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደረጃ የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
Read More...
የሰሜን ለንደን ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ከቶተንሃም ሆትስፐር ያደርጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡
ቶተንሃም የጨዋታ ብልጫ በወሰደብት የሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ክርስቲያን ሮሜሮ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ መምራት ቢችልም ሰን ሁንግ ሚን ቶተንሃምን አቻ አድርጎ የመጀመሪያውን አጋማሽ አንድ አቻ አጠናቅቀዋል፡፡…
አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን ሰበረች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የዓለም የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በመስበር አሸነፈች፡፡
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ53 ሰከንድ በመግባት ነው ክብረወሰኑን የሰበረችው።
ኬኒያዊቷ አትሌት ብሪግድ ኮስጌይ በፈረንጆቹ 2019 በ2 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ከ4 ሰከንድ በመግባት ይዛው…
ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ተጋጣሚውን ኖቲንግሃም ፎረስትን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ሲቲ÷ ፊል ፎደን እና ኤርሊንግ ሃላንድ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነው ተጋጣሚውን የረታው፡፡
ሮድሪ በ46ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር ክርስታል ፓላስ…
ሉሲዎቹ ከቡሩንዲ አቻቸው ጋር ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታው 9 ሰዓት ከብሩንዲ አቻው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም አካሂደዋል ።
በዚህም ሉሲዎቹ በመጀመሪያው አጋማሽ በረድኤት አስረሳኸኝ ጎል ተጋጣሚያቸውን 1 ለ 0 መምራት ችለው ነበር፡፡
ሆኖም በሁለተኛው አጋማሽ የብሩንዲ ሴቶች ብሄራዊ…
ጁሌያን ኔግልስማን የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የባየርሙኒክ አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በአንድ ዓመት ኮንትራት የጀርመን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል፡፡
የ36 ዓመቱ አሰልጣኝ በቅርቡ የተሰናበቱትን የቀድሞው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በመተካት ነው ብሄራዊ ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት የተረከቡት፡፡
ከስምምነቱ በኋላ ኔግልስማን…
ፊፋ የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊፋ የካፍ ዞን የአፍሪካ ሀገራትን ወቅታዊ የደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚሁ የፊፋ ደረጃ መሰረት ኢትዮጵያ በካፍ እውቅና ስር ከሚገኙ 50 ሀገራት 42ኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ ከዓለም ደግሞ 142ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ሞሮኮ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ፣ሴኔጋል፣ቱኒዝያ፣አልጀሪያ፣እና ግብፅ በቅደም…