Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ዛሬ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የምትካፈልበት የ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ውድድር ምሽት 2 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡ በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ የሚገኘው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ስድስተኛው ቀኑን ይዟል፡፡ በዛሬው እለትም የ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ማጣሪያ ውድድር ምሽት 2 ሰዓት ላይ የሚካሄድ ሲሆን÷ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ሀጐስ ገ/ሕይወት እና በሪሁ አረጋዊ ኢትዮጵያን ወክለው እንደሚሳተፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
Read More...

በሴቶች የ5 ሺህ ሜትር እና የ3 ሺህ ሜትር መሠናክል ማጣሪያ ሁሉም አትሌቶች ለፍጻሜ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምሽቱን በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር እና 3 ሺህ ሜትር የሴቶች መሠናክል የማጣሪያ ውድድር የተሳተፉ ሰባት አትሌቶች ወደ ፍጻሜ አልፈዋል፡፡ በተደረገው የ5 ሺህ ሜትር የማጣሪያ ውድድር÷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 2ኛ እንዲሁም አትሌት እጅጋየሁ ታዬ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ከየምድባቸው ማጠናቀቃቸውን የአትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ…

አትሌት ሃብታሙ ዓለሙ እና ወርቅነሽ መለሰ የ800 ሜትር ማጣሪያውን አለፉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሃብታም ዓለሙ እና አትሌት ወርቅነሽ መለሰ በ800 ሜትር ማጣሪያ በተለያየ ምድብ 1ኛ እና 3ኛ ሆነው በማጠናቀቅ ለግማሽ ፍጻሜው አልፈዋል፡፡ ትዕግስት ግርማ ከምድቧ 6ኛ ሆና ማጣሪያውን በማጠናቀቋ ወደ ቀጣዩ ዙር ሳታልፍ ቀርታለች፡፡

ኢትዮጵያ ዛሬ በ3 የማጣሪያ ውድድሮች ትሳተፋለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያውን ሴቶች አትሌቶች የሚሳተፉበት የ800 ሜትር፣ 5 ሺህ ሜትር እንዲሁም 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ይካሄዳል፡፡ ከረፋዱ 5፡05 ላይ የሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ፣ ምሽት 2፡02 ላይ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ማጣሪያ እንዲሁም ምሽት 2፡53 ላይ የሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ማጣሪያ ይካሄዳል፡፡ በ800 ሜትር…

ኢትዮጵያ የምትካፈልባቸው 2 የፍጻሜ ውድድሮች ምሽት ላይ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትካፈልባቸው የሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር እና የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሠናክል የፍጻሜ ውድድሮች ዛሬ ምሽት ላይ ይካሄዳሉ፡፡ ምሽት 4፡31 ላይ በሚካሄደው የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ይጠበቃሉ፡፡ እንዲሁም ምሽት 4፡42 ላይ በሚካሄደው የወንዶች 3…

በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዥ 3ኛ ደረጃን ይዛለች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው 19ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ባለፉት ሁለት ቀናት በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያ በ4 ሜዳሊያዎች 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች አሜሪካ በ3 ወርቅ፣ 2 ነሃስ እና በአንድ ብር ቀዳሚውን ደረጃ ስትይዝ ስፔን በሁለት የወርቅ ሜዳሊያ 2ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡…

በወንዶች 10 ሺህ ሜትር አትሌት ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳልያ አስገኘ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀንጋሪ ቡዳፔስት 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። በውድድሩ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት በሪሁ አረጋዊ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል። ውድድሩን ዩጋንዳዊው አትአትሌት ጆሹዋ ቼፕቴጌ 1ኛ በመሆን አጠናቋል።