ስፓርት
የአዲስ አበባ ስታዲየም በመጪው ዓመት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ስታዲየም በመጪው ዓመት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ የአዲስ አበባ ስታዲየም የግንባታ ሒደትን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደገለፁት÷በ2013 ዓ.ም የእድሳት ስራው የተጀመረው የአዲስ አብባ ስታዲየም ሁለተኛ ምዕራፍ ግንባታ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል፡፡
የስታዲየሙ ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ 65 በመቶ መድረሱን የገለፁት ሚኒስትሩ÷ በ2016 ዓ.ም…
Read More...
ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ30ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና 0 ለ 0 ተለያይተዋል፡፡
የቡድኖቹ ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም 9፡00 ላይ ተከናውኗል፡፡
ቡድኖቹ ነጥብ መጋራታቸውን ተከትሎም በግብ ክፍያ ተበላልጠው በእኩል 43 ነጥብ 4ኛ እና 5ኛ ደረጃ ላይ…
ማሰን ማውንት ማንቼስተር ዩናይትድን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን አማካይ ማሰን ማውንትን በይፋ አስፈርሟል፡፡
የላንክሻየሩ ክለብ ማሰን ማውንትን በአምስት ዓመት ኮንትራት ነው ያስፈረመው፡፡
ለአማካዩ ዝውውር 60 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ መደረጉን ጠቅሶ ቢ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡
ማውንት በቼልሲ ቆይታው 195 ጊዜ ተሰልፎ 33 ጎሎችን ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡
የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኮከብ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ሆነዋል።
በዚህ መሰረትም ቢኒያም በላይ እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፉዓድ ፈረጃ ፣ያሬድ ባየህና አለልኝ አዘነ ከባህር ዳር ከተማ፣ ባሲሩ ኡመር ከኢትዮጵያ መድኀን እንዲሁም ጌታነህ ከበደ ከወልቂጤ ከተማ በእጩነት ቀርበዋል፡፡…
በስቶኮልም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዊዲን ስቶኮልም በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች ድል ቀንቷቸዋል።
የ2023 የዳይመንድ ሊግ 7ኛው ዙር ውድድር በስቶኮልም የተካሄደ ሲሆን በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ተከታተለው በመግባት አሸንፈዋል።
በዚህ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ውድድር…
ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ጨዋታ እየቀረው የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስን ከሀድያ ሆሳዕና ያገናኘው የ29ኛ ሳምንት ጨዋታ÷ 9፡00 ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀድያ…
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና እና ለገጣፎ ለገዳዲ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ29ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ኢትዮጵያ ቡና እና ለገጣፎ ለገዳዲ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ከሊጉ መውረዱን ያረጋገጠው ለገጣፎ ለገዳዲ ከጥሩ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ጋር ሲዳማ ቡናን 3 ለ 2 መርታት ችሏል።
ካርሎስ ዳምጠው፣አማኑኤል አረቦ እና ሱለይማን ትራኦሬ የለገጣፎ ጎሎችን…