Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሞሮኮ እና ክሮሺያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍቢ ሲ) አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ ካናዳን 2 ለ 1 በማሸነፍ እና ክሮሺያ ያለምንም ግብ ከቤልጂየም ጋር አቻ በመለያየት ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል፡፡ ሞሮኮ ከምድቧ 7 ነጥብ በመያዝ በቀዳሚነት እንዲሁም ክሮሺያ ደግሞ አምስት ነጥብ በመያዝ ነው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉት፡፡ በኳታር አስተናጋጅነት እየተካሔደ በሚገኘው 22ኛው የዓለም ዋንጫ በምድብ ሥድስት የተደለደሉት ሞሮኮ እና ካናዳ ምሽቱን ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡ በዚሁ መሠረት ሞሮኮ ካናዳን 2 ለ1 በመርታት ከሴኔጋል በመቀጠል ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለች…
Read More...

በዛሬው የዓለም ዋንጫ ጀርመን ከኮስታሪካ የምታደርገው ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበበ፣ ሕዳር 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ ዛሬ ከምድብ አምስት እና ስድስት ወደ ጥሎ ማለፉ የሚቀላቀሉ ቡድኖችን የሚለዩ ጨዋታዎች ይከናወናሉ፡፡ በዚህም መሰረት በምድብ አምስት ጀርመን ከኮስታሪካ ምሽት አራት ሰዓት ላይ የሚደርጉት ጨዋታ ከወዲሁ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት በዚሁ ምድብ ጃፓን ከስፔን…

ፈረንሳይ እና አውስትራሊያ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዋንጫው ፈረንሳይ እና አውስትራሊያ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል። ማምሻውን 12 ሰአት በተካሄደው ጨዋታ ፈረንሳይ በቱኒዚያ 1 ለ 0 ብትሸነፍም ምድቡን እየመራች ጥሎ ማለፉን ተቀላቅላለች። ከዴንማርክ የተጫወተችው አውስትራሊያ 1 ለ 0 በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 21 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዋልያዎቹ ለሚሳቱፉበት የቻን ውድድር ለ42 ተጫዋቾች ጥሪ መደረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። በአሰልጣኝ ወበቱ አባተ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አልጄሪያ ላይ ለሚደረገው የአፍሪካ ሀገራት ቻምፒዮንሺፕ (ቻን) ማለፉ ይታወሳል። አሰልጣኙ ለቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ እና ተጫዋቾች በየክለባቸው…

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲውን ክለብ አል ናስር ለመቀላቀል መስማማቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፖርቹጋላዊው አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የሳዑዲውን ክለብ አል ናስር ለመቀላቀል መስማማቱን ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው፡፡ እንደ ሚረር እና ደይሊ ሜይል ዘገባ ሮናልዶ በአመት 173 ሚሊየን ዩሮ ይከፈለዋል የተባለ ሲሆን ይህም ሮናልዶን የዓለማችን ውዱ ተከፋይ ያደርገዋል። ሮናልዶ ከፔርስ ሞርጋን ጋር ካደረገው…

አርጀንቲና የዓለም ዋንጫ ቆይታዋን የሚወስነውን ወሳኝ ጨዋታ ምሽት ታደርጋለች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታሩ ዓለም ዋንጫ ዛሬ የምድብ ሦስት እና አራት የመጨረሻ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ፡፡ በምድብ አራት ቱኒዚያ ከፈረንሳይ እንዲሁም አውስትራሊያ ከዴንማርክ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በምድብ አራት ፈረንሳይ ስድስት ነጥብ በመያዝ ከምድቡ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፏን አስቀድማ ስታረጋግጥ አውስትራሊያ ሦስት ቱኒዚያ…

በዓለም ዋንጫ አፍሪካዊቷ  ሴኔጋል  እና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር ዓለም ዋንጫ ምሽት 12 ሰዓት ኔዘርላንድስ ከኳታር እንዲሁም ሴኔጋል ከኢኳዶር ጨዋታቸውን አድርገዋል፡፡ በጨዋታው አፍሪካዊቷ ሴኔጋል  ኢኳዶርን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ኔዘርላንድስ ኳታርን 2 ለ 0 አሸንፋለች፡፡ በዚህም ሴኔጋል እና ኔዘርላንድስ ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን…