ስፓርት
ወልቂጤ ከተማ እና ኢትዮጵያ መድን ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎችን አስተናግዷል።
ከምሳ በኋላ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ በአዲሱ የወውድድር አመት ሁለተኛ ድሉን አስመዝግቧል፡፡
ክትፎዎቹ ባህርዳር ከተማን በተመስገን በጅሮንድ ድንቅ ግብ 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡
10 ሰአት ላይ በተካሄደውና ሰባት ጎሎች በተቆጠሩበት ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ መድን አርባምንጭ ከተማን 4 ለ 3 አሸንፏል።
በጨዋታው አሸናፊ ፊዳ እና ተመስገን ደረሰ (2) ለወላይታ ዲቻ ሲያስቆጥሩ፥ ብሩክ ሙሉጌታ፣…
Read More...
ሊግ ኩባንያው በኢትዮጵያ መድን፣ ድሬዳዋ እና ወልቂጤ ከተማ ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2015 (ኤፍ ቢሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኩባንያ በ2015 ዓ.ም በ1ኛ ሳምንት ውድድሮች ላይ በታዩ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
የሊግ ኩባንያው ውድድር አመራርና ሥነስርዓት ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ በሳምንቱ በተደረጉ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የሥነ ምግባር ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ…
በሀትሪክ የታጀበው የማንቼስተር ደርቢ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኧርሊንግ ሃላንድ እና ፊል ፎደን ሀትሪክ የሠሩበት የማንቼስተር ደርቢ በሲቲ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ዛሬ በተካሄደ የእንግሊዝ ፕሪሚየርሊግ ማንቼስተር ሲቲ ማንቼስተር ዩናይትድን 6ለ 3 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን ጎሎች÷ ፊል ፎደን በ8ኛው፣ በ44ኛው እና በ72ኛው ደቂቃ እንዲሁም…
በለንደን እና ጣልያን በተካሄዱ የተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን የማራቶን፣ በጣልያን የግማሽ ማራቶን እና የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሮችን ኢትዮጵያ በበላይነት አጠናቀቀች፡፡
በለንደን የተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር በአትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊነት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
አትሌት ያለምዘርፍ እርቀቱን 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በሆነ ሰዓት…
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታዎች ወልቂጤ ከተማና ባሕር ዳር ከተማ አሸነፉ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታዎች ወልቂጤ ከተማና ባሕር ዳር ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ የውድድር ወቅቱን በድል ጀምረዋል።
ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተጀምሯል።
በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ አምበሉ ጌታነህ ከበደ በ50ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ድንቅ የቅጣት…
የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተሳታፊ ሀገራት አዲስ አበባ እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተሳታፊ ሀገራት አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ከተሳታፊ ሀገራት መካከል የብሩንዲ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ከ17 ዓመት ብሔራዊ ቡድኖች ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸውን…
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 1ለ 0 ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ቡድኑ ባሳለፍነው ሐሙስ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻው ጋር ያደረገውን የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት መለያየቱ…