ስፓርት
ምሽት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት ምሽት በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በምሽት በተካሄደ የእንትሪም ግማሽ ማራቶን በወንዶች ጀማል ይመር 59 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ በመግባት አንደኛ ደረጃን ይዞ ሲጨርስ፥ በዚሁ ርቀት ሌላኛው አትሌት ተስፋሁን አካልነው 4ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
በሴቶች ደግሞ ያለም ዘርፍ የኋላው 1 ሰዓት ከ4 ደቂቃ በመግባት ስታሸንፍ፥ጸሀይ ገመቹ 1 ሰዓት ከ5 ደቂቃ በመግባት 2ኛ ደረጃን ይዛ ርቀቱን ጨረሳለች፡፡
አውስትራሊያ በተደረገ የግማሽ…
Read More...
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ ውጤት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ ይፋ ሆኗል፡፡
የወንዶች የአግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ምርጫ በዛሬው እለት ተካሂዷል፡፡
በምርጫው ውጤት መሰረት አዲሱ ቃሚሶ ፣ ዶ/ር ዳኛቸው ንገሩ ፣ ሸረፋ ደሌቾ ፣ ሙራድ አብዲ ፣ አሰር ኢብራሂም እና ኡጁሉ…
አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ
ዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።
የፕሬዜዳንታዊ ምርጫው የድምፅ ቆጠራ ከደቂቃዎች በፊት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በውጤቱም ላለፉት አራት ዓመታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በፕሬዝዳንትነት የመሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ 94 ድምፅ በማግኘት በድጋሚ ተመርጠዋል።
በእጩ ተወዳዳሪነት…
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያን 3ኛ ደረጃ ይዞ አጠናቀቀ
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ በሦስተኛነት አጠናቀቀ።
በማጣሪያው ላይ ኢትዮጵያን የወከለው ንግድ ባንክ ዛሬ በአዛም ኮምፕሌክስ ባደረገው የደረጃ ጨዋታ የርዋንዳውን ኤ ኤስ ኪጋሊን 3 ለ 1 በማሸነፍ ሦስተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
አረጋሽ ካልሳ፣ ሀሳቤ…
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የምርጫ ጠቅላላ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በጉባዔው ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን…
ዋሊያዎቹ በቻን ማጣሪያ ጨዋታ 0 ለ 0 ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን ማጣሪያ ከሩዋንዳ አቻው ጋር 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይቷል፡፡
የቻን የመጨረሻ ዙር የመጀመሪያ ማጣሪያ ጨዋታ በታነዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በጫወታውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ አቻው ጋር 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይቷል፡፡
የመልሱ ጨዋታ ከቀናት በኋላ…
“ማሜሎዲ ሳንዶውንስ”ን ለተቀላቀለው አቡበከር ናስር አቀባበል ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካውን ማሜሎዲ ሳንዶውንስ የተቀላቀለውን ኢትዮጵያዊ ፕሮፌሽናል የእግር ኳስ ተጫዋች አቡበከር ናስር በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ሙክታር ከድር አቀባበል አደረጉለት፡፡
በአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በደቡብ አፍሪካ የተባበሩት ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አመራሮችም እንደተገኙም ነው የተመለከተው፡፡…