ስፓርት
በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ሻምፒዮን ሆናለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ ) በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ሻምፒዮን ሆናለች።
ሴኔጋል ግብፅን በመለያ ምት 4 ለ 2 በማሸነፍ ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ አንስታለች።
ጎል ያልተቆጠረበት የ120 ትንቅንቅ ወደ መለያ ምት አምርቶ የቲሪንጋ አንበሶቹ ሴኔጋል ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በጨዋታው ብልጫ የነበራት ሴኔጋል የመጀመሪያ ዋንጫዋን በማንሳት የትሪንጋ አንበሶቹ በያውንዴ ደምቀው አምሽተዋል፡፡
ካሜሮን ቡርኪናፋሶን በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡
በፌቨን ቢሻውና ሚኪያስ ዓየለ
Read More...
የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታን ደቡብ አፍሪካዊው ቪክቶር ጎሜዝ በዋና ዳኝነት ይመሩታል
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካዊው ኢንተርናሽናል አልቢትር ቪክቶር ጎሜዝ ዛሬ ሴኔጋልና ግብፅ የሚያደርጉትን የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ እንዲዳኙ በካፍ መመረጣቸው ተገልጿል።
ደቡብ አፍሪካዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ቪክቶር ጎሜዝ ከፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ በደቡብ አፍሪካ ሊግ የሚደረጉ ታላላቅ ጨዋታዎችን መርተዋል፡፡
ቪክቶር…
በአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀቀች።
ምሽቱን ለደረጃ የሚደረግ ፍልሚያ በአዘጋጇ ሀገር ካሜሮንና በቡርኪናፋሶ መካከል ተደርጓል።
ጨዋታው 3 አቻ በመጠናቀቁ ወደ መለያ ምት ያመራ ሲሆን፥ በመለያ ምት ካሜሮን ቡርኪናፋሶን 5 ለ 3 በመርታት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።…
ዛሬ ምሽት ቡርኪናፋሶ እና ካሜሮን ለደረጃ ይጫወታሉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው የፍሪካ ዋንጫ መርሃ ግብር መሠረት ቡርኪና ፋሶ እና አዘጋጇ ካሜሮን ለደረጃ ይፋለማሉ።
ጨዋታው ምሽት 4፡00 ላይ በያውንዴ አህመዱ አሂጆ ስቴዲዬም ይካሄዳል።
በሌላ በኩል የአፍሪካ ዋንጫ ነገ ፍፃሜውን የሚያገኝ ሲሆን፥ በዕለቱም ግብጽ እና ሴኔጋል ለዋንጫ ይፋለማሉ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ…
ግብጽ ወይስ ሴኔጋል – ሁለቱን የሊቨርፑል ኮከቦች በተቃራኒው ያገናኘው የፍጻሜ ጨዋታ
https://www.youtube.com/watch?v=ylQXjMOjUIs
በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች፡፡
የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 1 ለ 0 ቢሸነፍም ዛሬ በተደረገው ጨዋታ 2 ለ0 በማሸነፍ 2 ለ 1 በሆነ ድምር ዉጤት ወደ መጨረሻው ዙር ማለፍ ችሏል፡፡…
በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛንያን ዛሬ ታስተናግዳለች
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ2022 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 4ኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዛሬ ከቀኑ በ10፡00 ታንዛንያን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ታስተናግዳለች።
ቀደም ሲል አስተያየታቸዉን የሰጡት የቡድኑ አስልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል፥ ከታንዛኒያ መልስ ቡድኑ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆቱን ተናግረዋል፡፡
ይህ ከ20 ዓመት…