Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ካፍ የቱኒዚያን ይግባኝ ውድቅ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) አወዛጋቢ የዳኝነት ስርዓት በተስተዋለበት የማሊ እና ቱኒዚያ ጨዋታ ቱኒዚያ ያቀረበችውን ይግባኝ ዉድቅ ማድረጉን ካፍ አስታውቋል። የጨዋታው የመሀል ዳኛ ጃኒ ሲካዝዌ ጨዋታው ከተጀመረ ጀምሮ አወዛጋቢ ውሳኔዎችን ከመወሰን በተጨማሪ፥ የ90 ደቂቃ መደበኛ ሰዓት ከማለፉ በፊት ጨዋታውን ሁለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ፊሽካቸውን አሰምተዋል፡፡ አወዛጋቢው የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ ብቻ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶች የተሰጡ ሲሆን፥ ስምንት የተጨዋች ቅያሬዎችም ተደርገውበታል፡፡ በማሊ የ 1-0 ሽንፈት…
Read More...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት በተደረገ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በካሜሩን አቻው 4 ለ1 ተሸነፈ፡፡ በካሜሮን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከካሜሩን አቻው ጋር አድርጓል፡፡ በዚህም ዋልያዎቹ 1 ለ 1 በሆነ…

ዛሬ ምሽት ዋሊያዎቹ ከካሜሩን አቻቸው ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ ምሽት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከካሜሩን አቻው ጋር ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋል፡፡ በካሜሮን አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ ምሽት 1 ሰዓት ላይ ተጠባቂ የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከካሜሩን አቻው ጋር ያደርጋል፡፡ ዋልያዎቹ ባሳለፍነው እሁድ በምድቡ…

ያሬድ ባየህ ብሔራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ይሰለፋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ ያሬድ ባየህ ከአንድ ጨዋታ ቅጣት በኋላ ለብሔራዊ ቡድኑ እንደሚሰለፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ገለፀ፡፡ የብሔራዊ ቡድኑ ተከላካይ ያሬድ ባየህ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኬፕ ቬርዴ ጋር ባደረገው ጨዋታ 12 ኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ መውጣቱ ይታወሳል። በዚህም አንድ ጨዋታ…

ሀገር አቀፍ የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ውድድር ተጀመረ

አዲስ አበባ ጥር 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች የእግር ኳስ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ተጀመረ። የፖን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች ውድድር ተተኪ ስፖርተኞችን ለመፍጠር ዕድል እንደሚሰጥ ተገልጿል። የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታዎች አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ…

በአፍሪካ ዋንጫ ሞሮኮ ጋናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካሜሮን አፍሪካ ዋንጫ የሁለተኛ ቀን መርሃ ግብር ዛሬ ቀጥሎ ተካሂዷል፡፡ በዚህም ሞሮኮ ጋናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የመጀመሪያዋን ሶስት ነጥብ አስመዝግባለች፡፡ የሞሮኮ ብሄራዊ ቡድንን  ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቦፋል በ82ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከኬፕ ቬርዴ ጋር አድርጓል። በውጤቱም ኢትዮጵያ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፋለች። በጨዋታው ጅማሬ ላይ ባዬ ያሬድ በቀይ ካርድ መውጣቱን ተከትሎ ዋልያዎቹ በጎዶሎ ተጫውተው ለመጨረስ ተገደዋል። ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ…