Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ዕጣ አወጣጥ ስነ ስርአት ዛሬ በዶሃ ተካሂዷል። በምድብ 1 አስተጋጇ ኳታር፣ ኔዘርላንድስ፣ ሴኔጋል እና ኢኳዶር፤ በምድብ 2 ደግሞ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ኢራን እና የዌልስ/ስኮትላንድ ወይም ዩክሬን አሸናፊ፤ በምድብ 3 አርጀንቲና፣ ሜክሲኮ፣ ፖላንድ እና ሳዑዲ አረቢያ፤ በምድብ 4 ፈረንሳይ፣ ዴንማርክ፣ ቱኒዚያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች/አውስትራሊያ ወይም የፔሩ አሸናፊ፤ በምድብ 5 ስፔን፣ ጀርመን፣ ጃፓን እና የኮስታሪካ ወይም…
Read More...

ክላረንስ ሴዶርፍ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ ይመጣል

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የኔዘርላንድስ አማካይ ክላረንስ ሴዶርፍ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ጋር አዲስ አበባ ይመጣል። የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ሚያዚያ 2 ቀን ቅዳሜ በሸራተን አዲስ ከቀኑ 7 ሰአት ጀምሮ በሚካሄድ ስነ ስርአት በተመልካች ይጎበኛል። ሴዶርፍም ከዋንጫው ጋር ሚያዚያ 2 ቀን ቅዳሜ በሸራተን አዲስ የሚገኝ…

በወርሃዊው የፊፋ የአገራት ደረጃ ዋልያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ቀነሱ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወርሃዊው የፊፋ የሀገራት ደረጃ ሰንጠረዥ ዋልያዎቹ ሁለት ደረጃዎችን ዝቅ ብለዋል፡፡   ዓለም አቀፉ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) በየወሩ የዓለም ሀገራትን የአግር ኳስ ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡   ለበርካታ ወራት በደረጃው አናት ላይ የነበረችው ቤልጂየም ደረጃዋን ለብራዚል በማስረከብ ወደ…

አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰኢድ ሲዳማ ቡናን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው አጥቂ ሳላዲን ሰኢድ ሲዳማ ቡናን በይፋ መቀላቀሉን ክለቡ አስታውቋል፡፡   በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ በጉልህ ከሚነሱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ሰላዲን ሰኢድ ሲዳማ ቡናን በይፋ መቀላቀሉ ተረጋግጧል፡፡   ከሙገር ስሚንቶ በኋላ ረጅም ዓመታትን በቅዱስ ጊዮርጊስ ያሳለፈው ሳላዲን…

ሴኔጋል እና ካሜሮን ለ2022 ዓለም ዋንጫ ማለፋቸውን አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 21፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴኔጋል እና ካሜሮን ለ2022 ዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ተወካይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ሴኔጋል በፍፃሜው ያገኘቻትን ግብፅን በድጋሚ በመለያ ምት በማሸነፍ ለኳታሩ 2022 ዓለም ዋንጫ ጨዋታ ማለፏን አረጋግጣለች። በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ ሴኔጋል ካይሮ ላይ በግብፅ 1 ለ…

16ኛ ሳምንት ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ነገ በአዳማ ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕርሚየር ሊግ ነገ በሚካሄዱ መርሃግብሮች ይጀምራል፡፡ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ በሚደረገው ጨዋታ÷ 9 ሰዓት ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማ እንዲሁም 12 ሰዓት ላይ ደግሞ ፋሲል ከነማ ከሀዲያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን ያደረጋሉ፡፡ የስታዲየም…

የአማራ ክልል ለቅድመ ዝግጅት ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ቅድመ ዝግጅት የአማራ ክልል ላወጣው ወጪ ካሳ እንደሚከፍል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በደብዳቤ እንዳስታወቀው÷ 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በባህርዳር ከተማ እንዲካሄድ ውሳኔ በማሳለፍ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል፡፡…