Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች፡፡   የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 1 ለ 0 ቢሸነፍም ዛሬ በተደረገው ጨዋታ 2 ለ0 በማሸነፍ 2 ለ 1 በሆነ ድምር ዉጤት ወደ መጨረሻው ዙር ማለፍ ችሏል፡፡   በአበበ ቢቄላ ስታዲዮም በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያን የማሸነፊያ ግቦች ረዴት አስረሳኸኝ አስቆጥራለች።   በሚኪያስ አየለ
Read More...

በሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛንያን ዛሬ ታስተናግዳለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በ2022 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ 4ኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ኢትዮጵያ ዛሬ ከቀኑ በ10፡00 ታንዛንያን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ታስተናግዳለች። ቀደም ሲል አስተያየታቸዉን የሰጡት የቡድኑ አስልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል፥ ከታንዛኒያ መልስ ቡድኑ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆቱን ተናግረዋል፡፡ ይህ ከ20 ዓመት…

ግብፅ ካሜሩንን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫው የፍጻሜ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በመለያ ምት ግብጽ ካሜሩንን 3ለ1 በማሸነፍ ከሴኔጋል በመቀጠል ለፍጻሜ ያለፈች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡ ግብፅና ካሜሩን ለፍታሜ ጥሎ ማለፍ ባደረጉት ጨዋታ ከ90 ደቂቃው ባሻገር የጭማሪውን 30 ደቂቃ ያለግብ በማጠናቀቃቸው አሸናፊው በመለያ ምት እንዲለይ ተደርጓል፡፡…

ጨዋታው ከጦርነት አያንስም፤ የካሜሩን ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ለዚህ ተዘጋጁ – ሳሙኤል ኤቶ ስለ ምሽቱ ጨዋታ

አዲስ አበባ፣ጥር 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ዛሬ ምሽት የሚደረገውን የግብፅ እና ካሜሮን ጨዋታ አስመልከቶ አንጋፋው እግር ኳስ ተጫዋች ሳሙኤል ኤቶ አስተያይቱን ሰጥቷል፡፡ ካሜሮናዊው የቀድሞው የባርሴሎና አጥቂ ሳሙኤል ኤቶ ቀደም ሲል በሰጠው አስተያየት፥ አሁን ላይ ሁላችንም ስለ አንድ ጉዳይ ብቻ ነው ምናስበው እሱም የዛሬ ምሽቱ ፍልሚያ ነው ብሏል።…

ኢትዮጵያዊዉ ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ባሳዩት የዳኝነት ብቃት አድናቆት አገኙ

አዲስ አበባ፣ጥር 26፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋል ቡርኪናፋሶን ስታሸንፍ ጨዋታዉን በመሀል ዳኝነት የመሩት ዳኛ ባምላክ ተሰማ ጨዋታዉን ለመምራት ባሳዩት ብቃት በአፍሪካ ዋንጫ ተመልካቾች እየተወደሱ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያዊዉ ኢንተርናሽናል ዳኛ ሁለት የፍፁም ቅጣት ምቶችን ከሰጡ በኋላ በተንቀሳቃሽ ምስል (VAR) በመታገዝ ዉሳኔዉ ትክክል…

ቱኒዚያ የብሔራዊ ቡድን አሠልጣኟን አሰናበተች

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ቱኒዚያ ከአፍሪካ ዋንጫ የግማሽ ፍፃሜ ማጣሪያ ከተሰናበተች በኋላ የብሔራዊ ቡድኑን አሠልጣኝ ሞንደሄር ኬቤየርን አሰናብታለች፡፡ አሠልጣኙ በኳታር የዓለም ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ውድድር ላይ ለመሳተፍ ሁለት ወራት ሲቀራቸዉ ነዉ ከብሔራዊ ቡድኑ የተባረሩት፡፡ ከነኀሴ 2019 ጀምሮ የቱኒዚያን ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝነት ሲመሩ የቆዩት…