Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግና ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፉ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ መቐለ 70 እንደርታ በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግና ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እንዲሳተፉ መወሰኑ ተገለፀ።   የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክሉት እንዲያሳውቅ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።   ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ የ2011 የፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ እንዲሳተፍ ሲወስን የጥሎ ማለፍ ዋንጫ ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ በኮንፌዴሬሽን…
Read More...

ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊው የኮቪድ 19 መከላከያ ጥንቃቄ በማድረግ እንደሚጀመሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ሲጀመሩ አስፈላጊው የኮቪድ 19 መከላከያ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢፊዴሪ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ። በትናንትናው ዕለት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ስፖርታዊ እንቅስቀሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ እንዲነሳ መወሰኑን ተከትሎ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን…

ፌዴሬሽኑ በፖላንድ ለሚካሄደው የዓለም ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌቶችን ለመምረጥ የ15 ኪ.ሜ ማጣሪያ ውድድር በሰንዳፋ አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን በፖላንድ ጊዲኒያ ጥቅምት 7 ለሚካሄደው የዓለም ግማሽ ማራቶን ውድድር የሚሳተፋ አትሌቶችን ለመምረጥ የ15 ኪሜ ማጣሪያ ውድድር በሰንዳፋ መስመር አካሄደ፡፡ ፌዴሬሽኑ በማጣሪያው ላይ አስር ወንድና አስር ሴት አትሌቶች መሳተፋቸው ተናግሯል፡፡ በውድድሩ የተካፈሉት አትሌቶች አምና በሀገር…

የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የቀድሞው ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ አራት ዓመት ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የቀድሞ ፕሬዚዳንት ላሚን ዲያክ በሙስና ጥፋተኛ ተብለው አራት ዓመት ተፈረደባቸው፡፡ የ87 ዓመቱ ላሚን ዲያክ ከሙስና በተጨማሪ በህገውጥ የገንዘብ ዝውውር ተጠያቂ ተደርገዋል፡፡ በአውሮፓውያኑ 2012 የለንደን ኦሊምፒክ መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡ በዘህ ውድድር ላይ አበረታች…

አበበ ቢቂላ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ በመሮጥ የወርቅ ሜዳሊያ ካስገኘ ዛሬ 60ኛ ዓመቱን ያዘ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሻምበል አበበ ቢቂላ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ በመሮጥ የወርቅ ሜዳሊያ ካስገኘ ዛሬ 60ኛ ዓመቱን ያዘ። የዛሬ 60 ዓመት አበበ ሳይጠበቅ ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለመላው አፍሪካ በጥቁር ሕዝብ ታሪክ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ለማስገኘት በቅቷል። የሮሙ ድል አፍሪካውያን ሀ ብለው የረጅም ርቀት ውድድሮች የበላይ እንዲሆኑ…

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን በሬድዮ በቀጥታ ለማስተላለፍ ለሚፈልጉ ድርጅቶች ሊሸጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ዻጉሜን 5 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ በ2013 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን  የፕሪሚየር ሊግ ውድድር  በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ የኢትዮጵያን ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመ ህጋዊ ተቋም ነው ፡፡ በመሆኑም…

ሞ ፋራህ በኃይሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሸለ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአራት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ብሪታኒያዊው ሞ ፋራህ ብሩሴልስ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ለ13 ዓመታት በሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተይዞ የቆየውን ክብረ ወሰን አሻሻለ፡፡ በትውልድ ሶማሊያዊው የሆነው ሞ ፋራህ በአንድ ሰዓት ውስጥ 23 ነጥብ 33 ኪሎ ሜትር በመሮጥ ነው በኃይሌን ተመዝግቦ የነበረውን 21 ነጥብ 285…