ስፓርት
ዮሚፍ ቀጀልቻ ሄንግሎ ላይ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሆላንድ ሄንግሎ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር አሸነፈ፡፡
ዮሚፍ ርቀቱን 13 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ ከ84 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ አጠናቋል፡፡
እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሐሰን በ10 ሺህ ሜትር አሸንፋለች፡፡
ሲፈን ከዚህ ቀደም በፓውላ ራድክሊፍ ተይዞ የነበረውን የአውሮፓን የ10 ሺህ ሜትር ርቀት ክብረወሰንን አሻሽላለች፡፡
በዚህ ርቀት ሲፈንን በመከተል ኢትዮጵያዊቷ ፀሐይ ገመቹ ሁለተኛ በመሆን አጠናቃለች፡፡
Read More...
አትሌት ለተሰንበት ግደይ አቀባበል ተደረገላት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስፔን ቫሌንሺያ የሴቶችን የ5 ሺህ ሜትር ክብረወሰን የሰበረችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ አቀባበል ተደረገላት፡፡
ለተሰንበት ከዋና አሰልጣኟ ኃይሌ እያሱ ጋር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ማርቆስ ገነቴ የኢትዮጵያ አትሌቶች…
ለተሰንበት ግደይ የ5 ሺህ ሜትር ክብረወሰንን በማሻሻል አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለተሰንበት ግደይ ስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ውድድር ክብረወሰን በማሻሻል አሸነፈች፡፡
የ22 ዓመቷ ለተሰንበት ርቀቱን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ጊዜ 14 ደቂቃ ከ6 ሰከንድ ከ62 ማይክሮሰከንድ ነው፡፡
ይህን ተከትሎም በሌላኛው ኢትዮጵያዊት አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የሴቶች የ5 ሺህ ሜትር ክብረ…
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በ22 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት እና የውድድር ስያሜ ለዲ ኤስ ቲቪ በ22 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ተሸጠ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩን በቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ለማስተላለፍ ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች ባወጣው ጨረታ መሠረት ሲያወዳድር መቆየቱ ተገልጿል፡፡…
የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 3 ይጀምራል
አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኢትዮጵያ የወንዶች እግር ኳስ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ታህሳስ 3 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ ይፋ አድርጓል።
የፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒው በኮቪድ ውስጥ ሆኖ የኢትጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለማስጀር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የቅደመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ…
40ኛው የለንደን ማራቶን ላይ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች አዲስ አበባ ሲገቡ አቀባበል ተደረገላቸው
አዲስ አበባ ፣መስከረም 26 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፕላቲኒየም ደረጃ በተሠጠው በ40ኛው የለንደን ማራቶን ላይ ውጤት ያስመዘገቡ አትሌቶች ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱም አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
በአቀባበሉ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ፣ የኢትዮጵያ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ተጫዋቾች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
ፌዴሬሽኑ ካሜሩን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት 40 ተጫዎች መጥራቱ ይታወሳል፡፡
ጥሪ ተደርጎላቸው ከተገኙ 36 ተጫዎቾች ውስጥም አምስቱ ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ብሏል፡፡
ቀሪዎቹ የቡድኑ…