ስፓርት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ተጫዋቾች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምስት ተጫዋቾች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
ፌዴሬሽኑ ካሜሩን ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት 40 ተጫዎች መጥራቱ ይታወሳል፡፡
ጥሪ ተደርጎላቸው ከተገኙ 36 ተጫዎቾች ውስጥም አምስቱ ኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል ብሏል፡፡
ቀሪዎቹ የቡድኑ አባላት ካፍ አካዳሚ ትናንት መግባታቸው ነው የተነገረው፡፡
ፌዴሬሽኑ ለእያንዳንዱ ተጫዋች የግል ህይወት ነጻነት ሲባል እና በስነ ልቦናም እንዳይጎዱ የተጫዋቾቹን ስም ይፋ…
Read More...
ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በለንደን ላስመሰገቡት ውጤት ምስጋና አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በለንደን በተካሄደው የወንዶች ማራቶን አሸናፊ ለሆኑ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን አስደናቂት ውጤት አስመዝግበዋል ሲሉ አስፍረዋል።
አትሌት ሹራ ቅጣታ የ2020 የለንደን ማራቶንን በማሸነፉ…
የለንደን ማራቶንን ኢትዮጵያዊው ሹራ ቅጣታ ቶላ አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሲጠበቅ የነበረውን የለንደን ማራቶን ኢትዮጵያዊው ሹራ ቅጣታ ቶላ ሲያሸንፍ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሲሳይ ለማ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
ሹራ ቅጣታ ቶላ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ41 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ውድድሩን ያሸነፈው።
ውድድሩን ሊያሸንፍ እንደሚችል በከፍተኛ ሁኔታ ሲጠበቅ የነበረው ኢሊውድ…
ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውጪ መሆኑን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ከለንደን ማራቶን ውጪ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ቀነኒሳ በቀለ ከውድድሩ ውጪ የሆነው በግራ ባቱ ላይ ባጋጠመው ጉዳት እንደሆነ ተናግሯል፡፡
አትሌቱ ይህን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንዳሰፈረው ውድድሩን ባለመሳተፌ በጣም አዝናለሁ ብሏል፡፡
ለውድድሩ ዝግጅት እንዳደረገ የገለፀው አትሌቱ…
ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን የወንዶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ፡፡
አሰልጣኙ ቡድኑን ለቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ እና የዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ማጣሪያ የማሳለፍ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።
በስምምነቱ መሰረት ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የተጣራ 125 ሺህ ብር…