Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ጠ/ሚ ዐቢይ ለዋልያዎቹ መልካም ውጤት ተመኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) መልካም ውጤት ተመኙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉን አስፍቷል ሲሉ አስፍረዋል። ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው ያስገኙት ድል ትልቅ አርአያነት አለው ብለዋል። በቀጣዩ ጨዋታቸው መልካሙን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ በማለት ለቡድኑ መልካም ውጤት ተመኝተዋል። የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን…
Read More...

የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌዴሬሽን አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  “የዩኒቨርስቲ ስፖርት ዓለምን ለመቀየር” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌዴሬሽን አጠቃላይ ስብሰባ በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና የተለያዩ ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ የፌዴሬሽኑ አባላት…

ደሴቷ ሀገር ኮሞሮስ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደሴቷ ሀገር እና 900 ሺህ ህዝብ ብቻ ያላት ኮሞሮስ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ  ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች። ከቶጎ ብሄራዊ ቡድን ጋር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት መለያየቷን ተከትሎ ደሴቷ ሀገር በካሜሩን አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ አልፋለች። 5 ጨዋታዎችን አድርጋ 9 ነጥብ በመሰብስ በምድቧ በግብ ክፍያ…

ዋልያዎቹ ማዳጋስካርን 4 ለ 0 በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማዳጋስካርን 4 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ኮቲዲቫር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ ውጤት እስከሚታወቅ የደረጃ ሰንጠረዡን በ9 ነጥብ መምራት ጀምረዋል። ግቦቹን…

ቻድ ከ2021ዱ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ታገደች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቻድን ከ2021ዱ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ማገዱን አስታወቀ፡፡ ካፍ ውሳኔውን ያስተላለፈው የሀገሪቱ መንግስት የቻድን እግር ኳስ ማህበር በይፋ ማፍረሱን ተከትሎ ነው፡፡ የቻድ ብሄራዊ ቡድን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከናሚቢያ እሁድ ደግሞ ከማሊ ጋር የነበረውን ጨዋታ…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አንድ ጨዋታ እየቀረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡ በ17ኛው ሳምንት የሊጉ ውድድር አዳማ ከተማን 2 ለ 1 መርታቱን ተከትሎ ነው ሻምፒዮናነቱን ያረጋገጠው፡፡ በውድድር ዘመኑ ቡድኑ 43 ነጥቦችን መሰብሰቡን ከንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ…