Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀዋሳ ከተማን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፈ። የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ሮቢ ንግላንዴ በ33ኛው ደቂቃ ፣ ጌታነህ ከበደ በፍጹም ቅጣት ምትና በጨዋታ በ39ኛ እና 43ኛው ደቂቃዎች ላይ እና ዳዊት ታደሰ በ55ኛው ደቂቃ በራሱ ግብ ላይ አስቆጥረዋል። የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ እና የማስተዛዘኛ ጎል ብሩክ በየነ በፍፁም ቅጣት ምት በ80ኛው ደቂቃ ላይ ማስቆጠር ችሏል።
Read More...

አትሌት ወንድወሰን ከተማና እዮብ ኃብተስላሴ አበረታች ቅመሞች በመጠቀማቸው ከውድድር ታገዱ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስፖርት አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግ) በመጠቀም የህግ ጥሰት በፈፀሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ፡፡ አትሌት ወንድወሰን ከተማ ማሞ እና አትሌት እዮብ ኃብተስላሴ ጎሳ የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) በመጠቀም ተጠርጥረው ጊዜያዊ እገዳ ላይ ሆነው ጉዳያቸው ሲጣራ መቆቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ አበረታች…

ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና 644ኛ ጎሉን በማስቆጠር የፔሌን ክብረ ወሰን አሻሻለ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሊዮኔል ሜሲ ለባርሴሎና 644ኛ ጎሉን በማስቆጠር ለአንድ ክለብ ከፍተኛ ጎል በማስቆጠር በፔሌ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን አሻሻለ። አርጄንቲናዊው አጥቂ ትናንት ምሽት ሪያል ቫያዶሊድ ከባርሴሎና ባደረጉት የስፔን ላሊጋ የባርሴሎናን ሶስተኛ ግብ በ65ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠር የፔሌን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል።…

የሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ውድድር በጃፓኗ ካሳማ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጃፓኗ ካሳማ ከተማ ለጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ መታሰቢያ ለሁለተኛ ጊዜ ተካሂዷል። ውድድሩን ያስጀመሩት በጃፓን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ካሳ ተ/ብርሃን እና የማራቶን ሯጭ እና አሰልጣኝ ኮማንደር አበበ መኮንን መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በዚህ የ21 ኪሎ ሜትር የጎዳና…

በሴካፋ ዋንጫ የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ዋንጫ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን በማሸነፍ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ17 ዓመት በታች የሶስተኛ ደረጃ ለመያዝ ከጅቡቲ ጋር ባደረገው ጨዋታ 5 ለ 2 አሸንፏል፡፡ በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ከ17 ዓመት…

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ የ2020 የአሜሪካ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አምበል የሆነችው ናኦሚ ግርማ የ2020 የአሜሪካ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሆና ተመርጣለች። በዚህ ዓመት ለዋናው ብሔራዊ ቡድን መመረጥ የቻለችው የተከላካይ መስመር ተጫዋቿ በ2019 የኮሌጅ ቡድኗ ስታንፎርድ ዋንጫ እንዲያነሳ የረዳች ሲሆን የ PAC-12 ምርጥ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች…

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በታዛኒያ አቻው በመለያ ምት ተሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በታዛኒያ አቻው በመለያ ምት ተሸነፈ። ይህን ተከትሎ ከምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ  የፍፃሜ ጨዋታ ውጭ ሆኗል። 90 ደቂቃው በ1 ለ 1 በሆነ በመጠናቀቁ ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት ሄደዋል። በመለያ ምቱ የታንዛኒያ ከ17 ዓመት…