ስፓርት
ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ለወላይታ ድቻ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ አብነት ደምሴ አስቆጥሯል።
ፈረሰኞቹ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ30 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ29 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በጨዋታው ከረጅም ጊዜ የጉዳት ቆይታ በኋላ ወደ ሜዳ ተመልሶ የነበረው የወላይታ ድቻው ተጨዋች መልካሙ ቦጋለ በዛሬው…
Read More...
በ2026 የዓለም ዋንጫ በፍጻሜ ጨዋታ የእረፍት ሰዓት የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚኖር ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ላይ በፍጻሜው ዕለት አዳዲስ ዝግጅቶች እንደሚቀርቡ የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ተናግረዋል።
በዚህ መሰረትም በፍጻሜው ጨዋታ በእረፍት ሰዓት በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚቀርብ ነው የገለጹት፡፡
የዓለም ዋንጫ ከጀመረበት ከፈረንጆቹ 1930 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ…
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሊቨርፑል ከ ፒኤስጂ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዛሬ ምሽት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ ሊቨርፑልን ከፒኤስጂ የሚያገናኘው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት እየተመራ በቀጥታ 16ቱን የተቀላቀለው የእንግሊዙ ክለብ ሊቨርፑል ወደ ፓሪስ አቅንቶ ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር በፓርክ ደ ፕሪንስ ምሽት 5 ሰዓት…
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተጠባቂው የማድሪድ ደርቢ ዛሬ ምሽት ይደረጋል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ይደረጋሉ።
በዕለቱ ተጠባቂ መርሃ ግብር የወቅቱ ሻምፒዮን ሪያል ማድሪድ የከተማ ተቀናቃኙ አትሌቲኮ ማድሪድን ምሽት 5 ሰዓት በሳንቲያጎ ቤርናባው ያስተናግዳል።
በመድረኩ በፈረንጆቹ 2014…
ወላይታ ድቻ ኢትዮዽያ መድንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የኢትዮዽያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወላይታ ድቻ የሊጉን መሪ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
የወላይታ ድቻን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ በመጀመሪያው አጋማሽ ፀጋዬ ብርሃኑ አስቆጥሯል።
በአሰልጣኝ ገብረ መድን ኃይሌ የሚመሩት መድኖች ከተከታያቸው ሀዲያ ሆሳዕና ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 7…
20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በዓድዋ ከተማ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በትግራይ ክልል ዓድዋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን 20ኛውን የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር አስጀምረዋል።
በወንዶች ምድብ ሃጎስ ገብረሕይወት፣ ገመቹ ዲዳ እና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች መሳተፋቸውን የአትሌቲክስ…
ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ረፋድ በተደረገው ጨዋታ ሀብታሙ ታደሰ ለሲዳማ ቡና እንዲሁም ዳዋ ሁጤሳ (በፍፁም ቅጣት ምት) የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግቦችን አስቆጥረዋል፡፡
የ20ኛ ሳምንት መርሃ ግብሮች ከሰዓት ቀጥሎ…