Fana: At a Speed of Life!

ለተፈናቃዮች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሸዋ ሮቢትና ለደብረ ብረሃን ተፈናቃዮች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ ተደረገ፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከሰራተኞቹና ከአመራሩ እንዲሁም ከድርጅቶች ያሰባሰበውን ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ምግብ፣ አልባሳት፣ የንጽህና መጠበቂያ እና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ሸዋሮቢት ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተሬሳ ኢንሱስ፥ ድጋፉ ካለው ተፈናቃይ ቁጥር አንጻር በቂ ባይሆንም በተወሰነ ደረጃ እንደሚያግዝ ገልጸው ድጋፉ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ቅድሚያ በመስጠት በፍትሃዊነት ለተፈናቃዮች እንዲደርስ አስተባባሪዎች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

ነዋሪዎቹ ተረጋግተው ወደመደበኛ የዕለት ተዕለት ተግባራቸው እስኪመለሱ ድረስም ድጋፍን በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የከተማው አፈጉባኤ አቶ ግርማ ኃይሉ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ የዱከም ከተማ ሰላም የበጎ አድራጎት መህበር ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ዮሴፍ ክብሩ ÷በቀጣይም የድጋፉ መጠን በማሳደግ ተባብረን ለወገኖቻችን እንደርሳለን ብለዋል ፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው በአንድነት ስንቆም ችግሮቻችንን መሻገር እንችላለን ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.