Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ባደረሰው ጥቃት 759 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልሉ በአራት ዞኖችና 21 ወረዳዎች የሽብር ቡድኑ ባደረሰው ጉዳት 694 ትምህርት ቤቶች በከፊል እና 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በድምሩ 759 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል።
የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አሊ መሐመድ እንደገለጹት÷ የወደሙትን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባትና የትምህርት ሥራውንም ለማስቀጠል በክልሉ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትንና አመራሮችን ባካተታ መልኩ የተዋቀረ ቡድን ወደ ሥራ ገብቷል፡፡
ለመልሶ ጥገናውና ግንባታው የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ ተሰልቶ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም አብራተዋል፡፡
የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በመጠገንና በመገንባት የትምህርት አገልግሎትን ከማስቀጠል አንፃር ህብረተሰቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
የጭፍራ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ መሐመድ አብዱ በበኩላቸው÷ የትምህርት ቤቶቹ የጉዳት መጠን ሲታይ በተለይ በአፈጻጸማቸው ሞዴል በሆኑትና በአንጋፋ ትምህርት ቤቶች ላይ የከፋ መሆኑን ጠቅሰዋ፡፡
ይህ ድርጊት ወራሪው ሃይል ለአፋር ህዝብና ልጆች ያለውን የጠላትነት ጥግ ያሳየ ነው ማታቸውን ከትምህርት ሚኒቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.