የዳያስፖራውን አገራዊ ተሳትፎ የሚያጎለብቱ የተለያዩ መርሃ ግብሮች ተዘጋጅተዋል-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚያራምዱትን የተዛባ ፖሊሲ አስተካክለው ወደ ትክክለኛ የግንኙነት መስመር እንዲገቡ በ2022 ሰፊ ዲፕሎማሲያዊ ስራ ይሰራልም ተብሏል።
የውጭ ግንኙነት መርሆች ሁለት መሆናቸውን የጠቀሰው መግለጫው ፥እነርሱም የአገሪቱን ሉአላዊነት ማስጠበቅና የዜጎችን መብቶች ማስጠበቅ ዋነኞቹ መሆናቸው ተመላክቷል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ጀፍሪ ፌልትማን ከኢትዮጵያ ውጭ ከሌሎች አገራት መሪዎች ጋር የሚያደርጉት ንግግር ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል።
ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ ሲካሄድ የነበረው ሶስትዮሸ ድርድር በሱዳን አለመረጋጋት የተነሳ መቀጠል አለመቻሉ ተነስቷል፥ በሱዳን እየታየ ያለው አለመረጋጋት አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ኢትዮጵያ ድጋፏን እንደምትቀጥል ተገልጿል።

-2.7x lower