Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ከግማሽ ሚሊየን በላይ ህዝብ  የሚጠቀምባቸው  የጤና ተቋማት ወድመዋል- የክልሉ ጤና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  በአፋር ክልል ከግማሽ ሚሊየን በላይ የሚሆን ህዝብ ይጠቀምባቸው የነበሩ የጤና ተቋማት መውደማቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለጸ።

የአሸባሪው ቡድን በአፋር ክልል አካሂዶት በነበረው ወረራ 14 ወረዳዎችን ያካለለ  ጥቃትና ጉዳት አድርሷል።

በዚህም በክልሉ እስካሁን 52 ጤና ኬላዎችን፣ 21 ጤና ጣቢያዎችና አንድ ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ ያወደሙ ሲሆን፥ የደረሰው ጥፋት በገንዘብ ሲተመን   1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የሚገመ ት እንደሆነ የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል።

ፋና ቴሌቪዥን  ቅኝት ባደረገባቸው የጭፍራ፣ ዋኣ አማ እና የዳርሳጊታ ጤና ጣቢያዎች የሽብር ቡድኑ በህክምና መሳሪያዎች፣ ቁሳቁሶች ፥  በርና መስኮቶች ሳይቀር ከፍተኛ ውድመትና ዝርፊያ ፈጽሟል።

የወደሙና የፈረሱ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም በፌደራልና በክልል የጋራ  ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን፥ እስካሁን 14 ጤና ተቋማት ብቻ የመልሶ ማቋቋም ተደርጎላቸዋል።

አካባቢው ለወባ እና ለሌሎች በሽታዎች የተጋለጠ በመሆኑ የታማሚዎች ቁጥር እየጨመረ  ሲሆን፥ የህክምና አገልግሎቱን በሙሉ አቅም ለማከናወን የመሳሪያ እና የመድሃኒት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ  አለመኖሩም ነው የተገለጸው።

የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ያሲን  ሃቢብ እንደገለጹት ፥ የአፋር ማህበረሰብ ወደ ጤና ጣቢያ መጥቶ እንዲታከም  ለማድረግ ረዥም ጊዜ የወሰደ መሆኑን ገልጸው፥ አሁን በኝብር ቡድኑ የደረሰው ጉዳት ወደ ኋላ የመለሰ እና ማህበረሰቡን ክፉኛ የጎዳ ነው ብለዋል።

በርካታ ሰዎች ወደ ህክምና በመጓዝ ላይ እያሉ ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት አቶ ያሲን፥ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ህዝብ  ከህክምና አገልግሎት ውጪ  ሆኗል ብለዋል።

አሁንም ማህበረሰቡ በጤና ችግር  የከፋ ጉዳት  እንዳይደርስበት መልሶ የመገንባት ስራው እና  የሚመለከታቸው አካላት  ድጋፍ   እንዲፋጠን ጠይቀዋል።

በፍሬሕይወት ሰፊው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.