ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ሊሰጥ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ሊሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ፡፡
ውይይቱም በተቋማት ተጠያቂነትና የመረጃ ፍሰትን ለመዘርጋት እንዲሁም ውጤታማ እና ቀልጣፋ ሥራ እንዲያከናወኑ ያስችላል በተባለ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ረቂቅ መዋቅር ላይ ያተኮረ ነው።
በመንግስትም ሆነ በግል የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ወደሚፈለገው ደረጃ ከፍ ለማድረግ በቀጣይ የትምህርት ዘመን የመውጫ ፈተና ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ሊሰጥ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርቱ ማህበረሰብ ከፖለቲካ ነፃ ሆነው ሃሳባቸውን የሚያንሸራሸሩባቸው ተቋማት መሆን እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀት፣ የምርምርና የአዳዲስ ሃሳቦች መፍለቂያ ከመሆናቸው አንፃር ተልዕኳቸውን በብቃትና በውጤታማነት ለመፈፀም ይችሉ ዘንድ የተጀመረው የመዋቅር ሪፎርም ሥራ አንዱና ወሳኝ አካል መሆኑንም ነው የጠቀሱት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!