Fana: At a Speed of Life!

ኦሮሚያ ባንክ እና ግሎባል አሊያንስ ለድርቅ ተጎጂዎች 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ባንክ እና ግሎባል አሊያንስ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 10 ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብ እህል እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉ የተደረገው በኦሮሚያ ክልል ቦረናና ጉጂ ዞኖች እንዲሁም በሱማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ለከፍተኛ ጉዳት ለተዳረጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው።
የኦሮሚያ ባንክ ፕሬዝደንት አቶ ተፈሪ መኮንን፥ ባንኩ ለአርብቶ አደሮቹ ችግር ለመድረስና ለማቋቋም 2 ሺህ ኩንታል የምግብ እህል እርዳታ ለሁለቱ ዞኖች በአምስት ሚሊየን ብር ገዝቶ አስረክቧል ብለዋል፡፡
ግሎባል አሊያንስ ፎር ዘራይት ኦፍ ኢትዮጵያ በበኩሉ ፥ በሱማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ግምታቸው አምስት ሚሊየን ብር የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
በአርቲስት ታማኝ በየነ የሚመራው ሉዑክ በዉጪ ሀገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያሰባሰበውን ሩዝና ዘይት ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ቢሮ አስረክቧል።
ድርጅቱ ከዚህ ቀደም በአሸባሪ ቡድኑ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ያወሱት አርቲስት ታማኝ በየነ፥ አሁንም በድርቅ እየተጎዱ ከሚገኙ ወገኖች ጎን እንደሚቆም አስታውቀዋል፡፡
በቢቂላ ቱፋ እና በምንያህል መለሰ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.