ኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች በወልቂጤ ከተማ ለሚገነባው 11ኛ ቅርንጫፍ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ጥር 29፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኃይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች በወልቂጤ ከተማ ለሚገነባው 11ኛ ቅርንጫፍ የመሰረት ድንጋይ ዛሬ ተጥሏል፡፡
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር በሆቴል ኢንቬስትመንት ለመሰማራት በተረከበው 5 ሺህ 352 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ግንባታ ለማስጀመር በደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡
የሪዞርቱ ግንባታ በግማሽ ቢሊየን ብር እንደሚከናወን የገለፀው÷ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ግንባታውን በአጭር ጊዜ በመጀመር በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግሯል።
አትሌቱ በደቡብ ክልል ለሚያከናውናቸው የኢንቬስተመንት ስራዎች የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ርዕሰ መስተዳደሩ ርስቱ ይርዳው መናገራቸውን ደሬቴድ ዘገቧል።