ከአሻባሪው ትህነግ ጋር የተደረገው ውጊያ ጀግና አመራርና አባላትን ማፍራት የተቻለበት ነው -ሜ/ጄኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ከአሻባሪው ትህነግ ጋር የተደረገው ውጊያ ከፍተኛ ልምድ የተገኘበት እና ምርጥ ጀግና አመራርና አባላትን ማፍራት የተቻለበት እንደነበር የምስራቅ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ፍቃዱ ፀጋዬ ተናገሩ።
ሜጀር ጄኔራል ፍቃዱ ÷ጠላት የህዝብ ማዕበል አስነስቶ የኢትዮጵያ ትልቁ የወጪና ገቢ ንግድ የሚካሄድበትን የሚሌ መስመር ለመቁረጥ ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ በጀግኖች የዕዙ አባላት እና የተቋሙ የሠራዊት ክፍሎች ተጋድሎ አለመሳካቱን አውስተዋል፡፡
በግንባሩ በተካሄደው ውጊያ አሸባሪው ትህነግ አለመጠን ይተማመንባቸው የነበሩ ክፍሎቹ ተደምስሰውበታል፤ ከፍተኛ ቁሳዊና ሰብዓዊ ኪሳራም ደርሶበታል ብለዋል።
ከፍተኛ የሰው ሃይል በፕሮፓጋንዳም ሆነ በማስገደድ አሰልፎ የቻለውን ያህል ሙከራ ቢያደርግም “እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም ” ያሉ የዕዙ አባላት በቅንጅት ባደረጉት ታጋድሎ የአሸባሪውን ከንቱ ህልም ቅዠት አድርገውታል ነው ያሉት።
ከዚህ ባለፈም ፍልሚያው ቀጣይ ለሚኖረው ማንኛውም ግዳጅ ትልቅ አቅም የሚሆኑ ጀግኖች እንዲፈጠሩ አስችሏል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!