Fana: At a Speed of Life!

የተቀናጁ አገልግሎቶችን ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን እንቀጥላለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተቀናጁ አገልግሎቶችን ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን የምንቀጥል ይሆናል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንዳሉት÷ ሀገራዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መሠረታዊ የሆነ የባህል ለውጥ ያስፈልጋል።

ካቀድናቸው አምስት የልማት ምሰሶዎች መካከል ቴክኖሎጂን ለአገልግሎት ዘርፉ እንደ ዋነኛ መሣሪያ በመጠቀም፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናን እና ተደራሽነትን ለማሻሻል በቁርጠኝነት እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።

‎መሶብ የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ የጀመርነው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም በመሶብ አገልግሎቶች የታየው ከፍተኛ የደንበኞች እርካታ የዚህን የሥራ ሞዴል ውጤታማነት በግልጽ አረጋግጧልም ነው ያሉት።

ይህም አሠራሩን ይበልጥ ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን እንደሚያመላክት ገልጸዋል።

ዛሬ በይፋ የተመረቀው የመሶብ የሞባይል አገልግሎትም የዚሁ ቀጣይነት ያለው የሥራ እንቅስቃሴ አካል ነው ብለዋል።

‎ዜጎቻችን ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙና ትርጉም ያለው የጊዜ ቁጠባ እንዲያገኙ ለማስቻል እነዚህን የተቀናጁ አገልግሎቶች ይበልጥ ተደራሽ የማድረግ ሥራችንን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉም አመላክተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.