ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአዳማ ከተማ የተገነባውን የጫጩት ማስፈልፈያ ፋብሪካ በይፋ ስራ አስጀመሩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ የተገነባውን የኢትዮ ችክን የጫጩት ማስፈልፈያ ፋብሪካ መርቀው ስራ አስጀመሩ።
በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ኢትዮ ችክን ጫጩት ማስፈልፈያ ፋብሪካ በ150 ሚሊየን ብር የተገነባ ሲሆን፥ በሳምንት 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ጫጩቶችን የማስፈልፈል አቅም አለው ተብሏል።
ፋብሪካው በዶሮ እርባታ ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋልም ነው የተባለው።
ከዚህ ባለፈም በአካባቢው የሚገኙ አርሶና አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision