የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለ2015 በጀት ዓመት ከ4 ቢሊየን 548 ሚሊየን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለክልሉ ለ2015 በጀት ዓመት የሚውል 4 ቢሊየን 548 ሚሊየን 413 ሺህ 147 ብር በጀት አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ከበጀቱ በተጨማሪ÷ የክልሉን ያልተማከለ የአካባቢ አስተዳደር ለማጠናከር የወጣውን አዋጅ ጨምሮ ዘጠኝ ረቂቅ አዋጆችና የተሻሻለው የአሠራርና አባላት ስነ ምግባር ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት በማድረግ አጽድቋል።
የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡቦንግ ኡቶው እንደገለጹት÷ ለበጀት ዓመቱ እንዲውል ከተያዘው በጀት ውስጥ 1 ቢሊየን 621 ሚሊየን 168 ሺህ 517 ብር በክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሸፈን ነው፡፡
እንዲሁም 2 ቢሊየን 927 ሚሊየን 244 ሺህ 630 ያህሉ ከፌደራል መንግሥት በድጎማ÷ ቀሪው ደግሞ ከተለያዩ ተቋማት የውስጥ ገቢ፣ ከዘላቂ ልማት ግቦች ማሳኪያ እና ከውጪ ከሚገኝ ዕርዳታ እንደሚሸፈን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!