ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽነሮች ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽነሮች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ፥ ሀገራዊ ምክክሩ ልዩነትን በመቀራረብ በመፍታት የመነጋገር ዕድልን ፈጥሮ ሀገርን ሰላማዊ የማድረግ አቅም እንዳለው ገልፀዋል፡፡
ህዝብ ተስፋ የሰነቀበት ሀገራዊ ምክክር እውንና ስኬታማ እንዲሆን የክልሉ መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍን እንደሚያደርግም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል፡፡
እስካሁን በኮሚሽኑ በኩል የተሰሩ ስራዎችን በሀገራዊ የምክክር ኮሚሽነሮች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተመስገን ይመር
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!