Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የ15 ሺህ 960 ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት የ15 ሺህ 960 ፕሮጀክቶች ግንባታ ተከናውኗል አለ የአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፡፡

የቢሮው ኃላፊ እናትአለም መለስ በሰጡት መግለጫ ÷ በበጀት ዓመቱ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 15 ሺህ 960 ፕሮጀክቶች ከነገ ጀምሮ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

ከተሰሩት ፕሮጀክቶች መካከል በዋናነት የሕዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ከ10 ሺህ በላይ ቤቶች መገንባታቸውን ነው የተናገሩት፡፡

በበጀት ዓመቱ የከተማዋን ነዋሪዎች የቤት ፍላጎት ለማሟላት የተገነቡት ቤቶች በመንግስት እና በሕብረተሰቡ ትብብር መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በአጠቃላይ የማሕበረሰቡን ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሚያግዙ የጤና፣ የትምህርት እና የመንገድ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል ነው ያሉት ሃላፊዋ።

የከተማዋን ወጣቶች ጥያቄ ለመመለስ 122 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የተገነቡ ሲሆን ÷ ለ366 ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡

በአረንጓዴ ልማት ሥራ በ517 ሔክታር ላይ 245 ፕሮጀክቶች የተገነቡ ሲሆን÷ ከእነዚህ መካከልም ፓርኮች፣ ፕላዛዎች እና የመንገድ አካፋዮች ይገኙበታል ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል 246 ኪሎ ሜትር የእግረኛ እና 141 ኪሎ ሜተር የብስክሌት መንገድ እንዲሁም 43 ኪሎ ሜትር የመሮጫ ትራክ እና 53 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ እና የመሸጋገሪያ ድልድዮች መገንባታቸውን አመልክተዋል፡፡

በወንድማገኝ ጸጋዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.