Fana: At a Speed of Life!

በቻን ማጣሪያ ላይ የሚካፈሉት ዋልያዎቹ ነገ ወደ ታንዛኒያ ያቀናሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ወደ ታንዛኒያ ያቀናል።

ዋልያዎቹ ከሩዋንዳ አቻቸው ጋር የፊታችን አርብ በታንዛኒያ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የመልሱ ጨዋታ በርዋንዳ ነሐሴ 29 ቀን እንደሚደረግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስብስብ ለዚህ ጨዋታ ይረዳው ዘንድ ከዩጋንዳ ብሄራዊ ቡድን ጋር ሁለት የአቋም መለኪያ ጨዋታዎች ማድረጉ ይታወሳል።

የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ውድድር በአልጄሪያ አስተናጋጅነት በመጭው ጥር ወር 2015 ዓ.ም  ይካሄዳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.