የካሜሩን ንግድ ምክር ቤት ልዑካን የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩትን ጎበኘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የካሜሩን ንግድ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩትን የስራ እንቅስቃሴና የስልጠና አካዳሚ ጎብኝቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት በቀለና ሌሎች የስራ ክፍል ሀላፊዎች ለልዑካን ቡድኑ የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በኢትዮጵያ እና በካሜሩን መካከል የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ላይ ያተኮረ ጉብኝት እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ሌሎች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ እያደረገ እንደሚገኝ የልዑካን ቡድኑ አባላት መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!