በአፋር ክልል ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኞች ይተከላሉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ10 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ ነው።
በክልሉ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በተገኙበት በዱብቲ ከተማ ተካሂዷል፡፡
አቶ አወል አርባ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ከባለፉት ዓመታት ልምድ በመውሰድ ለዘንድሮ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡
የክልሉን የተፈጥሮ ፀጋዎች በማልማት ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸው÷ ማሕበረሰቡ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሚያደርገውን ተሳትፎ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኡስማን መሀመድ በበኩላቸው÷ በክልሉ 10 ሚሊየን 250 ሺህ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን አንስተው 60 በመቶ የሚሆኑት ለምግብነት የሚውሉ ችግኞች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በካሊፋ ከድር