Fana: At a Speed of Life!

አዲስ አበባ በሕግና በሥርዓት እየተመራች እንደስሟ ውብ አበባ ትሆናለች – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ በሕግና በሥርዓት እየተመራች እንደስሟ ውብ አበባ ትሆናለች ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አዲስ አበባን የሚመጥኑ፣ ሕገወጥነትን በብቃት ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ የሪፎርምና የለውጥ ስራዎች ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።

ዛሬም የዚሁ ሁለንተናዊ ሪፎርም አካል የሆነው አዲስ የደንብ ልብስ የማስተዋወቅ ስራ መከናወኑን ነው የገለጹት፡፡

አዲስ አበባ በሕግና በሥርዓት እየተመራች እንደስሟ ውብ አበባ ትሆናለች ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.