Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ለ2019 የትምህርት ዘመን አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በክልሉ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አስፈላጊው ዝግጅት እየተደረገ ነው አለ።

በክልሉ በ2019 የትምህርት ዘመን ከ7 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር መታቀዱን የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ቢያዝን ተናግረዋል፡፡

የተማሪዎችን ምዝገባ ከነሐሴ 18 እስከ ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም ለማከናወን ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸው፤ መስከረም 5/2019 ዓ.ም ትምህርት እንደሚጀመር ተናግረዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን ከ4 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን ማስተማር መቻሉን አንስተው፥ በ2019 ዓ.ም ሦስት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

አራት የሁለተኛ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤቶችም በትምህርት ሚኒስቴር ግንባታቸው በመከናወን ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

በክልሉ በ2018 ዓ.ም ከ85 ነጥብ 5 በመቶ የ6ኛ ክፍል ተፈታኞች እንዲሁም 78 በመቶ የ8ኛ ክፍል ተፈታኞች 50 እና ከዚያ በላይ ነጥብ ማስመዝገባቸውን አመልክተዋል፡፡

1ሺህ 829 ትምህርት ቤቶች በአዲስ ግንባታ መጠናቀቁንም አስረድተዋል።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ1ሺህ 205 የአንደኛ፣ መካከለኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ138 ሺህ በላይ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

በደሳለኝ ቢራራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.