ስፓርት
ፈላጊ ክለብ ያጣው ዴሊ አሊ…
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአንድ ወቅት የዝውውር ሒሳቡ ወደ 100 ሚሊየን ዩሮ ከፍ ብሎ የነበረው እንግሊዛዊው ተጫዋች ዴሊ አሊ አሁን ፈላጊ ክለብ ለማግኘት ተቸግሯል፡፡
የ29 ዓመቱ የቶተንሃም የቀድሞ ተጫዋች ዴሊ አሊ በተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ቢያሳልፍም አሁን እሱን ለማስፈረም ፍላጎት ያለው ክለብ ሊገኝ አልቻለም፡፡
የሕይወት አጋጣሚ ባልጠበቀው መንገድ የወሰደችው ኮከብ እንደዛሬው ብቃቱ ሳይከዳው ብዙ ፈላጊ ክለቦች ነበሩት፡፡
ከዓመት ዓመት ምርጥ ብቃቱን እያጣ የመጣው ዴሊ አሊ በፈረንጆቹ 2023 አስቸጋሪ ጊዜ…
Read More...
ኢትዮጵያ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር የብር ሜዳልያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ውድድር የብር ሜዳልያ አገኘች።
ብርቱ ፉክክር በታየበት በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ በመውጣት ነው ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የብር ሜዳልያን ያስገኘው።
በውድድሩ ላይ አትሌት ሰለሞን ባረጋ ውድድሩን በ6ኛነት…
አትሌት ፍሬወይኒ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ለፍጻሜ አለፈች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ለፍጻሜ አለፈች።
በሁለት ምድቦች ተከፍሎ በተደረገው ማጣሪያ የምድቡ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ ማለፍ ችለዋል።
አትሌት ፍሬወይኒ በምድብ አንድ ባደረገችው ውድድር 4 ደቂቃ ከ1 ሴኮንድ…
ኒውካስል፣ ቦርንማውዝ እና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ4ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ኒውካስል፣ ቦርንማውዝ እና ፉልሃም ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
ቀን 11 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ኒውካስል ዎልቭስን 1 ለ 0፣ ቦርንማውዝ ብራይተንን 2 ለ 1 እንዲሁም ፉልሃም ሊድስ ዩናይትድን 1 ለ 0 አሸንፈዋል፡፡
ክሪስታል ፓላስ ከሰንደርላንድ እንዲሁም ኤቨርተን…
አርሰናል ኖቲንግሀም ፎረስትን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት መርሀ ግብር አርሰናል ኖቲንግሀም ፎረስትን 3 ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በሜዳው ኖቲንግሀም ፎረስትን ያስተናገደው አርሰናል ዙቢሜንዲ (ሁለት) እና ዮኬሬሽ ባስቆጠሯቸው ግቦች ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር የነሀስ ሜዳሊያ አገኘች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ የነሀስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በውድድሩ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ለሀገሯ የነሀስ ሜዳሊያ አምጥታለች።
በውድድሩ ኬንያዊቷ አትሌት ቢያትሪስ ቼቤት ቀዳሚ ስትሆን ጣሊያናዊቷ ናዲያ ባቶቼሌቲ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡…
አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ1 ሺህ 500 ሜትር ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ20ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።
በሶስተኛው ምድብ የተወዳደረችው አትሌቷ ውድድሩን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ነው ግማሽ ፍፃሜውን የተቀላቀለችው።
በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው አትሌት ሳሮን በርሄ 9ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ…