Fana: At a Speed of Life!

ለቀጣዮች 6 ወራት የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት አይቻልም – የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሐምሌ 2 ቀን 2015 እስከ ታኅሣሥ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር እና ተከራይን ማስወጣት እንደማይቻል አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

ቀደም ሲል ከሰኔ 2 ቀን 2015 እስከ ሕዳር 2015፣ ከሕዳር 2 ቀን 2015 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2015፣ ከመጋቢት 2 ቀን 2015 እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2015 ደንብ በማውጣት ከቤት ኪራይ ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ለመፍታት ጥረት መደረጉ ተገልጿል፡፡

አሁንም ደንቡ ለአራተኛ ጊዜ ለቀጣዮች ሥድስት ወራት መራዘሙን የአስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስለዚህ የቀበሌ አመራሮች፣ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች እና የፍትሕ አካላት የዚህን ደንብ ተፈፃሚነት እንዲያስከብሩም አስተዳደሩ አሳስቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.