የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በደብረ ብርሃን ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስ ምርመራ በደብረ ብርሀን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተጀመረ።
ሆስፒታሉ በቀን እስከ 96 ናሙናዎችን መመርመር ይችላል ነው የተባለው፡፡
የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ዳግም ሽመላሽ እንደገለጹት፥ ምርመራውን ለመጀመር የሚያስችል መሳሪያ ዝግጅትና የባለሙያ ስልጠና በመጠናቀቁ ሆስፒታሉ ናሙናዎችን ለመመርመር ዝግጁ ሆኗል ብለዋል።
በቀጣይም ተጨማሪ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የመመርመር አቅሙን እንደሚያሳድግ ተገልጿል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ጥበቡ አበራ ምርመራው መጀመሩ ለዞኑና አጎራባች አካባቢዎች የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል።
በአበበ የሸዋልዑል