የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት 500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር ተከላ መርሐ ግብር እየተሳተፉ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች 500 ሚሊየን ችግኝ በአንድ ጀንበር ተከላመርሐ ግብር በየካ ክፍለ ከተማ ፈረንሳይ 01 አካባቢ እያከናወኑ ነው፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ ሎሚ በዶ ÷ በኢትዮጵያ የተጀመረው የአረንጓዴ ልማት ዘመቻ ለአፍሪካ ብቻ ሣይሆን ለዓለም ተምሳሌት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡
የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ÷ የአረንጓዴ ልማትን እውን በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአየር ብክለት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ቀውስ ለመቀነስ ዘመቻው አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል።