ለአወሊያ የእርዳታና የልማት ድርጅት ህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለ 19 ወለል የአወሊያ የእርዳታና የልማት ድርጅት ህንጻ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡
የመሰረት ድንጋዩን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የዓለም ዓቀፍ ሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ሼህ መሀመድ ቢን አብዱልከሪም አል ኢሳ ናቸው፡፡
በስነ-ስርዓቱ ላይ ከንቲባ አዳነች÷ ለዘመናት ትውልድን በመደገፍ ለሚታወቀው አወሊያ የሚደረገው ይህ ድጋፍ የትብብር እና የአንድነት ማሳያ ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሼህ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ፣ የዓለም ዓቀፍ ሙስሊም ሊግ ዋና ጸሃፊ ሼህ መሀመድ ቢን አብዱልከሪም አል ኢሳ(ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ተጋዝባዥ እንግዶች ተገኝተዋል::