በምስራቅ ሀረርጌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ካሳዬ አበበ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንደገለጹት፥ በወረዳው ልዩ ቦታው ቀርሳ ድልድይ የጭነት ተሽከርካሪ ባጋጠመው የመገልበጥ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
ከሟቾች በተጨማሪ በሰባት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጸው፥ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በቱጂ አብዲ