የምስራቅ ዕዝ ለጅግጅጋ የገበያ ማዕከል የእሳት አደጋ ተጎጂዎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመከላከያ ሠራዊት የምስራቅ ዕዝ በጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን የገበያ ማዕከል በተከሰተው የእሳት አደጋ ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ተጎጂዎች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን የምስራቅ ዕዝ ዋና አዣዥ ሌተናል ጄኔራል መሀመድ ተሰማ በጅግጅጋ ከተማ ተገኝተው ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ማስረከባቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል፡፡
የእሳት አደጋው ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተቋቁሞ የተለያዩ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል።